Kishore Kumar Hits

Betty G - Birabiroye lyrics

Artist: Betty G

album: Wegegta


ቢራቢሮ
ልትበር ቶሎ
ውብ አበባ አይታ ኖሮ
አኮብኩባ ልትነሳ
አላወቀች ወይ ኩብኩባ
ቢራቢሮ
ነሽ አዎ
ስታዪው መልክሽ ግን ሌላ ሆኖ
ተስፋሽ ምነው ተመናምኖ
እውነት ተውሽ እንዴት አስተማምኖ
አባ ጨጓሬ ውስጥ ግን ሁሌ
አይኖርም ስሚኝ ዛሬ
ኸረ ቢራቢሮዬ ስከኝ ቀስ በይና
ባንዴ መች ይበረራል ሂደት አለውና
ኸረ ቢራቢሮዬ ስከኝ ቀስ በይና
ባንዴ መች ለውጥ ይመጣል ሂደት አለው ገና
ሀሳብሽን ብቻ አይቶ
ቢያነሳው ጨፍልቆ
ቢያጣብቅሽ ከመሬት ጥሎ
መብረር ግን አለ ጊዜው ደርሶ
ኸረ ቢራቢሮዬ ስሚኝ ቀስ በይና
ባንዴ መች ይበረራል ሂደት አለውና
ኸረ ቢራቢሮዬ ስከኝ ቀስ በይና
ባንዴ መች ለውጥ ይመጣል ሂደት አለው ገና
በቀለማት አብዶ በአበቦች ተከቦ
በመአዛ ታውዶ ከአንዱ አንዱ በሮ
ይታይሻል ክንፍሽ ሲበር በመናብሽ
የመለወጥ ህልምሽ ይላወስ በሆድሽ
ታዲያ ቢራቢሮ አይሆን ተቻኩሎ
ያልሆኑትን ሆኖ ሂደትን ተጠልቶ
ብዬ ብነግራት ልቧን ልመልሳት
ከድካም ከጥፋት ልብ ብዬ ሳያት
እቺ ቢራቢሮ እኔ ሆኜ ኖሮ
ኸረ ቢራቢሮዬ ስከኝ ቀስ በይና
ባንዴ መች ይበረራል ሂደት አለውና
ኸረ ቢራቢሮዬ ስከኝ ቀስ በይና
ባንዴ መች ለውጥ ይመጣል ሂደት አለው ገና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists