መስኩ ተራራው ሸንተረር ጋራው
የአምላክ ጥበብ ነው በአንቺ የታየው
የአየሩ ምቾት ሁሌ የሚናፈቅ
ቅርሳ ቀርሱማ ልብ የሚሰርቅ
ይህ ነው ወይ ሀገር ማለት
ይህስ ብቻ ነው የምቱለት
የተፎከረው የተለቀሰው
የአባቶቻችን ደም የፈሰሰው
ለቡናው ነበር ወይስ ለእንጀራው
ለአራዊቱ ለአፈር ለሜዳው
አረ ይህ ነው ወይ ሀገር ማለት
ለዚህስ ብቻ ነው ወይ የምቱለት
አረ ይህ ነው ወይ ሀገር ማለት
ለዚህስ ብቻ ነው ወይ የምንምትለት
(ሀገሬ ሀገሬ) እንደተኛ እንዳንቀላፋም ሰው
(ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ) ሁሉ ከእንቅልፉ ሲነቃ
(ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ) ጉድ ነው የዛኔ
(ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ) በአንድ ላይ ሆኖ ሲነሳ
ሁሉም ይለወጣል (ሀገሬ)
መልካምም ይሆናል (ሀገሬ)
ሁሉም ተርፎት ያድራል (ሀገሬ)
ደስታችን ይበዛል (ሀገሬ)
ይጠፋል መጠላላት (ሀገሬ)
አንዱ አንዱን በአሽሙር መውጋት (ሀገሬ)
ሠው ለሠው መድሀኒቱ (ሀገሬ)
የዛኔ እንደሆን ሲገባው (ሀገሬ)
ሀገር ነው ወገን ወገን ነው ሀገር
ብዙ ነው ቋንቋው ግን አንድ ቤተሰብ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist