Kishore Kumar Hits

Betty G - Waga lyrics

Artist: Betty G

album: Wegegta


እቅድ አቅደን
ያላሰብነው ሲሆን
መንገድ ጀምረን
አደጋ ሲገጥመን
ግራ አጋብቶን ሁሉ ነገር
ትርምስምሱ ሲወጣ
የጠበቅነው ቀርቶ ያልጠበቅነው
በህይወታችን ሲመጣ
ዋጋ አለው
ህይወት ስታልፍ መከራ
እንደወርቅ እሳት ውስጥ
ተፈትና ስትሰራ
ዋጋ አለው
መታገስ አይደለም ለከንቱ
እንቁ ሲታሽ ነው እኮ የሚደምቀው ውበቱ
ጫን ፈጣን ያም ለሀያላን
ሞገስ ለአዋቂ
ሀብትም ለጠቢባን
አይደለም አይሆንም
እንደዛ ቢመስልም እንኳን
ጊዜ እና ግፍ ግን እነሱን ያገናኛቸዋል
ዋጋ አለው
ህይወት ስታልፍ መከራ
እንደወርቅ እሳት ውስጥ
ተፈትና ስትሰራ
ዋጋ አለው
መታገስ አይደለም ለከንቱ
እንቁ ሲታሽ ነው እኮ የሚደምቀው ውበቱ
(ሁሉን በጊዜው ባርኮ ስለሰራው)
(መጨነቅ ለምን ለሁሉም ጊዜ አለው)
(ሁሉን በጊዜው ባርኮ ስለሰራው)
(ተስፋ መቁረጥ ለምን ለሁሉም ጊዜ አለው)
ዋጋ አለው
መታገስ አይደለም ለከንቱ
እንቁ ሲታሽ ነው እኮ የሚደምቀው ውበቱ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists