ያኔ ድሮ በልጅነት
በነፃነት ውበት ለዛ
ጭቃ አብኩተን ቤት ሰርተናል
ተሞሽረን እንደዋዛ
የሳር ቅጠሉ ቃልኪዳናችን
መስክ ያዋለን በኛ አለም ግቡ ፍቅራችን
ለካ ያ ነበር ልክ መሆን
ፍቅርን መጋራት የእውነት ልብም ሳይሰስት
አለፈና ያ ሁሉ ጊዜ
በቁ ሲባል አደጉ ነፍስ አወቁ
እኔስ ተመኘሁ ያንን ዘመን
የልጅነት ውበቴን ሙሽርነቴን
የዘንባባው ቀለበቴ ይሁን ቅጣቴ
በቀና ልብ ያጠለቅነው የልጅነቴ
ሊያስታውሰኝ ቢመልሰኝ በሩቅ ትዝታው
እንደው ያንን የእውነት ዘመን ዳግም ስመኘው
ኡሁ ኦሆ አሀሀ አሄ
ኦሆሆ
ቃልኪዳን ትርጉሙን ካጣ
እኔነት ገዝፎ ሚዛን ከደፋ
መተዛዘን ይቅር ባይነት
እድሜ ሲጨምር በስለን ከጠፋ
የህይወት ቅምር ከሆነ የብቻ
ማስተዋል ሳያንስ ውጤቱ ባዶ
ነግሶ ፍራቻ
ለካ ያ ነበር ልክ መሆን
ፍቅርን መጋራት የእውነት
ልብም ሳይሰስት
ከሆነማ ነፍስ ማወቅ
ከራስ ተጣልቶ ሌላን ጎድቶ
ዞሮ መጨነቅ
እኔስ ተመኘሁ ያንን ዘመን
የልጅነት ውበቴን ሙሽርነቴን
የዘንባባው ቀለበቴ ይሁን ቅጣቴ
በቀና ልብ ያጠለቅነው
ያጠለቅነው
የልጅነቴ የልጅነቴ
ሊያስታዉሰኝ ቢመልሰኝ
በሩቅ ትዝታው
እንደው ያንን የእውነት ዘመን
የእውነት ዘመን
ዳግም ስመኘው
የዘንባባው ቀለበቴ
ይሁን ቅጣቴ
ይሁን ቅጣቴ ይሁን ቅጣቴ
በቀና ልብ ያጠለቅነው
ያጠለቅነው የልጅነቴ
ሊያስታውሰኝ ቢመልሰኝ
በሩቅ ትዝታው
አንደው ያንን የእውነት ዘመን
የእውነት ዘመን
ዳግም ስመኘው
የዘንባባው ቀለበቴ ይሁን ቅጣቴ
በቀና ልብ ያጠለቅነው የልጅነቴ
ቢመልሰኝ ቢመልሰኝ በሩቅ ትዝታው
እንደው ያንን የእውነት ዘመን
ዳግም ስመኘው
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist