Betty G - Minew lyrics
Artist:
Betty G
album: Manew Fitsum
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
መውደዴን መጠኑን ሳያውቀው
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
ውስጤ የሳለውን ምኞቴን አግኝቼ ቢያዘልቀኝ
የኔ ያልኩትን የሀሳቤን ሰው መርጦ ቢሰጠኝ
ያዩት ይመስል ጉዳቴን የብቸኝነቴን
በቃሽ ይሉኛል ይነግሩኛል ትቼ እንድኖር ቤቴን
አውቃለው የሰው ፍፁም እንደሌለው
ምችለው ተውት የኔው ጉዳይ ነው
ባልጠላም ለኔ አሳቢ መካሪ
እሻለው የኔን ችግር ተጋሪ
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
መውደዴን መጠኑን ሳያውቀው
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
ለኔ ያልታየኝ ያልገባኝ አንድ እንከን ቢኖርም
በአይኔ ካላየሁ አሉ ብዬ ቤቴን አልበትንም
ያዩት ይመስል ጉዳቴን የብቸኝነቴን
ይብቃሽ ይሉኛል ይመክሩኛል ትቼ እንድኖር ቤቴን
አውቃለው የሰው ፍፁም እንደሌለው
ምችለው ተውት የኔው ጉዳይ ነው
ባልጠላም ለኔ አሳቢ መካሪ
እሻለው የኔን ችግር ተጋሪ
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
መውደዴን መጠኑን ሳያውቀው
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
ምነው
ምነው
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
መውደዴን መጠኑን ሳያውቀው
ምነው ተይው ይለኛል ሰው
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist