Kishore Kumar Hits

Awtaru Kebede - Seww Negn Ina lyrics

Artist: Awtaru Kebede

album: Yikerta,Vol. 5


አንዳንዴማ
ሆዴን ፡ ባር ፡ ባር ፡ ሲለው ፡ ብቸኝነት ፡ ይዞኝ
አንዳንዴማ
የልብ ፡ ወዳጅ ፡ ያልኩት ፡ ከጐኔ ፡ ሲርቀኝ (፪x)
አዝናለሁ ፡ ሰው ፡ ነኝና (፪x)
የቀረው ፡ ግን ፡ ይቅርብኝ
አስቤ ፡ ልበል ፡ ቀና (፪x)
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ስኖር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
አንዴ ፡ ይሞላል ፡ ይጐላል
አንተ ፡ ከጐኔ ፡ ስላለህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል (፪x)
አሃ ፡ አንዴ ፡ ይሞላል ፡ አንዴ ፡ ይጐላል ፡ አሃሃ
አንተ ፡ ስላለህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
አሃ ፡ ቀኑ ፡ ይመሻል ፡ ቀኑ ፡ ይነጋል ፡ አሃሃ
አንተ ፡ ስላለህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
ጐዳናው ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ በሰው
በሰው ፡ ልብ ፡ ውስጥ ፡ ያለው
ትላንትናን ፡ ኖሮ ፡ ዛሬ ፡ ምኞት ፡ አለው (፪x)
ደግሞ ፡ ይናፍቀኛል ፡ ፊትህ ፡ ይናፍቀኛል (፬x)
አንዳንዴማ
ሆዴን ፡ ባር ፡ ባር ፡ ሲለው ፡ ብቸኝነት ፡ ይዞኝ
አንዳንዴማ
የልብ ፡ ወዳጅ ፡ ያልኩት ፡ ከጐኔ ፡ ሲርቀኝ (፪x)
አዝናለሁ ፡ ሰው ፡ ነኝና (፪x)
የቀረው ፡ ግን ፡ ይቅርብኝ
አስቤ ፡ ልበል ፡ ቀና (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists