Kishore Kumar Hits

Awtaru Kebede - Amelkihalehu lyrics

Artist: Awtaru Kebede

album: Yikerta,Vol. 5


ሞልቶ ፡ ለማይሞላ ፡ ለዚህ ፡ ዓለም ፡ ጉዳይ (፪x)
ጊዜ ፡ አላጠፋም ፡ ጐዶሎዬን ፡ ሳይ (፪x)
የበረከት ፡ ምንጩ ፡ መንገዱ ፡ ገብቶኛል (፪x)
ሁኔታው ፡ እያለ ፡ አምልከኝ ፡ ብሎኛል (፪x)
ልቤም ፡ እንዲህ ፡ ይለኛል
ኧረ ፡ ተነስ ፡ ይለኛል
አምልክ ፡ አምልክ ፡ ይለኛል
አመልክሃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ አመልክሃለሁ
አመልክሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)
ተይ ፡ አልኳት ፡ ነፍሴን ፡ ተይ ፡ እንጂ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ቆሞ ፡ ከደጅ
መዘመር ፡ ማምለክ ፡ ነው ፡ እንጂ (፪x)
አንተ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ
ዛሬም ፡ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ
ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በሕይወቴ
ያቆመኝ ፡ ፀጋህ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ
አሁን ፡ አሁንማ ፡ እየዋለ ፡ ሲያድር (፪x)
ይገርመኝ ፡ ጀመረ ፡ የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፪x)
ልቤን ፡ ያደረገው ፡ የዝማሬ ፡ ጓዳ (፪x)
ለካስ ፡ ተምሬ ፡ ነው ፡ የለብኝም ፡ ዕዳ (፪x)
ልቤም ፡ እንዲህ ፡ ይለኛል
ኧረ ፡ ተነስ ፡ ይለኛል
አምልክ ፡ አምልክ ፡ ይለኛል
አመልክሃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ አመልክሃለሁ
አመልክሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists