Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Yesew Eje Yelelebet lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yesew Eje Yelelebet


አዝ፦ አዳነኝ ፡ በፀጋው ፡ አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ነው
አምላክ ፡ በምህረቱ ፡ ባዘጋጀው ፡ መንገድ
በወንጌሉ ፡ እምነት ፡ ሰጠኝ ፡ ዳግም ፡ ልደት
በደስታ ፡ ከመዘመር ፡ ከማመስገን ፡ በቀር
እኔማ ፡ ምን ፡ ልከፍል ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር
የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት ፡ የእኔ ፡ ብሎ ፡ የሚያኮራ
በማመን ፡ የሚገኝ ፡ ጽድቅ ፡ የመስቀሉን ፡ ስራ
ፀጋው ፡ በእምነት ፡ ሆኖ ፡ አድኖኛል
እግዚአብሔር ፡ በልጁ ፡ ሕይወትን ፡ ሰጥቶኛል
ሁሉ ፡ ተፈጸመ ፡ በመስቀሉ
በሰላም ፡ እንድኖር ፡ በዘለዓለም፡ ፍቅሩ
ላመስግነው ፡ በዝማሬ ፡ ይኼን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ
ከጨለማ ፡ ለነጠቀኝ ፡ ከዚያ ፡ ክፉ ፡ ቦታ
ለወደደኝ ፡ ብርሃኑን ፡ ላበራ ፡ በሕይወቴ
መልካም ፡ ዜማ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ይክበር ፡ መድሃኒቴ
አምላክ ፡ አበጃጀው ፡ ዘለዓለሜን
አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጥቶ ፡ ክርስቶስ ፡ ብቃቴን
የዘለላእም ፡ ህብረት ፡ ከአብ ፡ ጋራ
አገኘሁ ፡ ልጅነት ፡ በክርስቶስ ፡ ስራ
ምሥጋናውን ፡ ልዘምረው ፡ ልናገር ፡ ወንጌሉን
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደሚያድን ፡ ላብስር ፡ ምስራቹን
የአምላክ ፡ ፍቃድ ፡ ኢኼ ፡ ሆኗል ፡ ሰዎን ፡ የሚያመልጡበት
በልጁ ፡ ደም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ጽድቅ ፡ አምነው ፡ ሚድኑበት
አዝ፦ አዳነኝ ፡ በፀጋው ፡ አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ነው
አምላክ ፡ በምህረቱ ፡ ባዘጋጀው ፡ መንገድ
በወንጌሉ ፡ እምነት ፡ ሰጠኝ ፡ ዳግም ፡ ልደት
በደስታ ፡ ከመዘመር ፡ ከማመስገን ፡ በቀር
እኔማ ፡ ምን ፡ ልከፍል ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር
የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት ፡ የእኔ ፡ ብሎ ፡ የሚያኮራ
በማመን ፡ የሚገኝ ፡ ጽድቅ ፡ የመስቀሉን ፡ ስራ
ምሥጋና ፡ ለአምላክ ፡ ፍቅር ፡ ለታደገኝ
እግሬን ፡ ከጨለማ ፡ መንገድ ፡ መለሰልኝ
ብርሃንን ፡ አሳየኝ ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉ
ተፈጸመ ፡ እንዳለ ፡ ጌታ ፡ በመስቀሉ
ባመሰግን ፡ ይበዛል ፡ ወይ ፡ እኔስ ፡ በየእለቱ
ቅኔን ፡ ብቀኝ ፡ ባሸበሸብ ፡ ብዘምር ፡ በቤቱ
እልልስ ፡ ብል ፡ በታላቅ ፡ ድምጽ ፡ ብጮህ ፡ እስከደስታ
ባጨበጭብ ፡ በመቅደሱ ፡ ለዚህ ፡ ክቡር ፡ ጌታ
አዝ፦ አዳነኝ ፡ በፀጋው ፡ አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ፡ ክስቶስ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ነው
አምላክ ፡ በምህረቱ ፡ ባዘጋጀው ፡ መንገድ
በወንጌሉ ፡ እምነት ፡ ሰጠኝ ፡ ዳግም ፡ ልደት
በደስታ ፡ ከመዘመር ፡ ከማመስገን ፡ በቀር
እኔማ ፡ ምን ፡ ልከፍል ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር
የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት ፡ የእኔ ፡ ብሎ ፡ የሚያኮራ
በማመን ፡ የሚገኝ ፡ ጽድቅ ፡ የመስቀሉን ፡ ስራ
አሃ (፬x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists