Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Lene Kebre lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yesew Eje Yelelebet


እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ
ውበት ፡ ሞገስ ፡ ዘውድ ፡ አክሊሌ (፪x)
ከቶ ፡ የማይርቅ ፡ በፍፁም ፡ ከአጠገቤ
ሚራራልኝ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ጥጋቤ
አይጓደል ፡ በፍፁም ፡ ምሥጋናዉ
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው
በቅዱሳን ፡ ጉባኤ ፡ ህብረት ፡ መሆን
ሊመሰገን ፡ ሊከብር ፡ ይገባዋል
መልካም ፡ መዓዛ ፡ ሆኖ ፡ ያርግ ፡ መሥዋዕቴ
ለወደደኝ ፡ አፍቃሪ ፡ መድሃኒቴ
ይድመቅ ፡ ጭብጨባው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታውም ፡ ይሰማ
ምሥጋና ፡ በአሪያም ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና (፪x)
የአገኘሁት ፡ ደህንነት ፡ ለመንፈሴ
ዳግም ፡ ልደት ፡ በደሙ ፡ መቀደሴ
የአምላክ ፡ መንግሥት ፡ ወራሽ ፡ አድርጐኛል
ባመሰግን ፡ ብዘምር ፡ ያንስብናል
ኦ ፡ ትበል ፡ ዛሬ ፡ ነፍሴ
ታምጣ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ውዳሴ ፡ ለንጉሡ
ጌታ ፡ ድንቅ ፡ ነውና (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ
ውበት ፡ ሞገስ ፡ ዘውድ ፡ አክሊሌ (፪x)
ከቶ ፡ የማይርቅ ፡ በፍፁም ፡ ከአጠገቤ
ሚራራልኝ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ጥጋቤ
አይጓደል ፡ በፍፁም ፡ ምሥጋናዉ
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው
ይዘምራል ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ክብሬ ፡ እያለ
በአምላኩ ፡ ሰው ፡ መሆኑን ፡ ያስተዋለ
ሕይወት ፡ የለውም ፡ ከጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሌላ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ክርስቶስ ፡ የእርሱ ፡ ተድላ
ይድመቅ ፡ ጭብጨባው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታውም ፡ ይሰማ
ምሥጋና ፡ በአሪያም ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists