Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Bersulay lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yesew Eje Yelelebet


የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣልኩና
ዝማሬን ፡ ዘመርኩኝ ፡ በገና ፡ ያዝኩና
አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ የልቤን ፡ ብነግረው
እግዚአብሔር ፡ መንገዴን ፡ መልካም ፡ አደረገው (፪x)
ማነው ፡ ተጨንቆ ፡ ሽቅብ ፡ ያደገ
የእራሱን ፡ ጸጉር ፡ ነጭ ፡ ያደረገ
ዛሬ ፡ በሆነው ፡ ነፍሴ ፡ አመስግኜው
ነገን ፡ አላውቅም ፡ ነገ ፡ የእርሱ ፡ ነው
የዘለዓለሙ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም ፡ ያዳነኝ
በዚህም ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እንዲያውቃል ፡ እንዲያኖረኝ
የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣልኩና
ዝማሬን ፡ ዘመርኩኝ ፡ በገና ፡ ያዝኩና
አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ የልቤን ፡ ብነግረው
እግዚአብሔር ፡ መንገዴን ፡ መልካም ፡ አደረገው (፪x)
ምግብን ፡ ከሰጠ ፡ ለሠማይ ፡ ወፎች
አምላክ ፡ ካሰበ ፡ ለምድር ፡ አበቦች
ለሰራኝማ ፡ ፈጥሮ ፡ በአምሳሉ
ተአምራት ፡ አለው ፡ ልቁም ፡ በቃሉ
ሃሳቤን ፡ በእርሱ ፡ ጥዬ ፡ እምነቴን ፡ ላጠንክረው
በኢየሱስ ፡ በጌታዬ ፡ ልቤን ፡ ላሳርፈው
የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣልኩና
ዝማሬን ፡ ዘመርኩኝ ፡ በገና ፡ ያዝኩና
አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ የልቤን ፡ ብነግረው
እግዚአብሔር ፡ መንገዴን ፡ መልካም ፡ አደረገው (፪x)
እርሱ ፡ ስለእኔ ፡ ያስባል ፡ ያለ
በጌታ ፡ ታምኖ ፡ ሸክሙን ፡ የጣለ
ማይነቃነቅ ፡ መሰረት ፡ ያለው
የጊዜው ፡ ወጀብ ፡ ያላናወጠው
ተመስገን ፡ ንገሥ ፡ ይላል ፡ በኢየሱስ ፡ ልቡ ፡ ያረፈ
ሁልጊዜ ፡ በአምላኩ ፡ ላይ ፡ እየተደገፈ
የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣልኩና
ዝማሬን ፡ ዘመርኩኝ ፡ በገና ፡ ያዝኩና
አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ የልቤን ፡ ብነግረው
እግዚአብሔር ፡ መንገዴን ፡ መልካም ፡ አደረገው (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists