Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Besemay Zufanu lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yesew Eje Yelelebet


አዝ፦ በሠማይ ፡ ዙፋኑ ፡ በመቅደሱ ፡ ያለው
የፍጥረት ፡ ፈጣሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
ዓይኑ ፡ እንዳየ ፡ አይፈርድ ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማ
በምክሩ ፡ ትክክል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱማ
ልብን ፡ ለይቶ ፡ የሚመረምረው
እንደሰው ፡ አይደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው
የሚያድን ፡ ነው ፡ ደግሞ ፡ የሚራራ
አቤቱ ፡ ማረኝ ፡ ላለ
ወደ ፡ እርሱ ፡ ለተጠጋ
ውድ ፡ ልጁ ፡ በመረቀልን ፡ በር
ወደ ፡ እርሱ ፡ መግባት ፡ አለ ፡ አሄ
ታላቅ ፡ ስሙ ፡ ይክበር
በምክሩ ፡ ጠቢብ ፡ ፍቅሩ ፡ የላቀ
በልጆቹ ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ የደመቀ
ምሥጋና ፡ ሞላ ፡ በማደሪያው ፡ ላይ
በመንጋው ፡ መልካም ፡ ማዳኑን ፡ ሲታይ
አዝ፦ በሠማይ ፡ ዙፋኑ ፡ በመቅደሱ ፡ ያለው
የፍጥረት ፡ ፈጣሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
ዓይኑ ፡ እንዳየ ፡ አይፈርድ ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማ
በምክሩ ፡ ትክክል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱማ
ልብን ፡ ለይቶ ፡ የሚመረምረው
እንደሰው ፡ አይደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው
ታናሹን ፡ ሰው ፡ ለክብር ፡ የሚያበቃው
የዳዊት ፡ የሙሴ ፡ አምላክ ፡ አሄ ፡ ለትሁቱ ፡ ጠበቃ
የወህኒውን ፡ መዝጊያ ፡ የሚሰብር
ለባሪያዎቹ ፡ ፈራጅ ፡ የሚሆን ፡ ሞገስ ፡ ክብር
አቢት ፡ እግዚአብሔር ፡ ስራው ፡ ድንቅ ፡ ነው
በመልካም ፡ ዜማ ፡ እስቲ ፡ እናምልከው
ክብሩ ፡ ይታወጅ ፡ በቤቱ ፡ መድረክ
የዘለዓለሙ ፡ አምላክ ፡ ይባረክ
አዝ፦ በሠማይ ፡ ዙፋኑ ፡ በመቅደሱ ፡ ያለው
የፍጥረት ፡ ፈጣሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
ዓይኑ ፡ እንዳየ ፡ አይፈርድ ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማ
በምክሩ ፡ ትክክል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱማ
ልብን ፡ ለይቶ ፡ የሚመረምረው
እንደሰው ፡ አይደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው
ተራሮችን ፡ ከላይ ፡ የሚያጠጣ
ለጻድቅ ፡ ለሃጥኡ ፡ አሄ ፡ ፀሐይን ፡ የሚያወጣ
ደረቁን ፡ ምድር ፡ የሚያለመልመው
ለታናሹ ፡ ሰው ፡ ብርታት ፡ እህ ፡ ሞገስ ፡ የሚሰጠው
ምሥጋናን ፡ ያምጡ ፡ ለእርሱ ፡ ያደሩ
በመንፈሱ ፡ ኃይል ፡ እየዘመሩ
የቤቱ ፡ ካህናት ፡ ምስክሮቹ
ስሙን ፡ ያክብሩ ፡ ታማኝ ፡ ባሮቹ
አዝ፦ በሠማይ ፡ ዙፋኑ ፡ በመቅደሱ ፡ ያለው
የፍጥረት ፡ ፈጣሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
ዓይኑ ፡ እንዳየ ፡ አይፈርድ ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማ
በምክሩ ፡ ትክክል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱማ
ልብን ፡ ለይቶ ፡ የሚመረምረው
እንደሰው ፡ አይደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists