Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Alem Atalay lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yesew Eje Yelelebet


ዓለሙም ፡ ምኞቱም ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ጠፊ ፡ ነው (፪x)
ዘለዓለም ፡ የሚያኖር ፡ የጌታን ፡ ፍቃዱን ፡ ማድረግ ፡ ነው (፪x)
አትታለል ፡ ልቤ ፡ በሚያብለጨልጨው
አዝ፦ ዓለም ፡ ዓለም ፡ አታልይ ፡ ናት (፪x)
እውነት ፡ ሕይወትና ፡ መንገድ ፡ ጌታ ፡ ኦ ፡ ለታመኑበት (፪x)
ከእሳት ፡ ተጠብቆ ፡ ለሚቆየው ፡ ዓለም (፪x)
ነፍሴ ፡ አትጓጊለት ፡ በፍፁም ፡ ይቅርብሽ ፡ ግድየለም (፪x)
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ብቻ
ከእሳት ፡ ከጨለማው ፡ በእምነት ፡ ማምለጫ (፪x)
አዝ፦ ዓለም ፡ ዓለም ፡ አታልይ ፡ ናት (፪x)
እውነት ፡ ሕይወትና ፡ መንገድ ፡ ጌታ ፡ ኦ ፡ ለታመኑበት (፪x)
ሕይወትና ፡ ተስፋ ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ (፪x)
በእውነት ፡ ለታመኑበት ፡ የሚሰጥ ፡ ከጌታ (፪x)
ይህን ፡ ያስተዋለ ፡ ጌታን ፡ ሙጥኝ ፡ ይላል
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ እድፈት ፡ እራሱን ፡ ያነጿል (፪x)
ዓለምን ፡ አትርፎ ፡ ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ቢያጐድላት
ከቶ ፡ ምን ፡ ሊጠቅመው ፡ ሁሌ ፡ ላይኖርባት
ብልጭልጯን ፡ ንቆ ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ የኖረ
እርሱ ፡ ነው ፡ ጠቢብ ፡ ሰው ፡ ያ ፡ ነው ፡ የተማረ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists