Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Yegebahalena lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yesew Eje Yelelebet


የጌታዎች ፡ ጌታ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ
የይሁድ ፡ አንበሳ ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ
በአምባ ፡ ላይ ፡ ፈረስ ፡ የምትቀመጠው
በክብር ፡ በግርማ ፡ የምትመለሰው
የዘለዓለም ፡ ተስፋችን ፡ ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የደህንነታችን ራስ
አዝ፦ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ
ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ
ፊትህ ፡ እንደፀሐይ ፡ በሃይል ፡ ያበራል
ፍቅርህ ፡ ከዕንቁ ፡ ይልቅ ፡ ልብን ፡ ይማርካል
ውበትህ ፡ ያማረ ፡ ክብርህን ፡ ተላብሰሃል
ተመስገን ፡ ጌታችን ፡ ተባረክ ፡ ብለናል
በምድር ፡ ክብር ፡ በሠማይ
ይገባሃልና ፡ መንገሥ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ
አዝ፦ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ
ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ
ብዙዎች ፡ ተገዙ ፡ ፍቅርህን ፡ ተረድተው
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያላ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ብለው
ድምጻቸው ፡ ተሰማ ፡ ከየማዕዘኑ
ቅኔን ፡ ተቀኙልህ ፡ በስምህ ፡ የዳኑ
ተመስገን ፡ ተባረክ ፡ ብለው
ዘምረው ፡ አይጠግቡም ፡ ደስታህ ፡ ኃይላቸው ፡ ነው
አዝ፦ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ
ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists