Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Alresawem lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yesew Eje Yelelebet


ጌታ ፡ በሕይወቴ ፡ ውዱ ፡ ያደረገውን ፡ መቼም ፡ አልረሳውም
እርሱ ፡ በሕይወቴ ፡ ፈቅዶ ፡ ያደረገውን ፡ መቼም ፡ አልረሳውም
አልረሳውም ፡ ያደረገልኝን ፡ አልረሳውም ፡ ለእኔ ፡ የሆነልኝን
አልረሳውም ፡ የአምላኬን ፡ ውለታ ፡ ዘወትር ፡ ልቀኝ ፡ ለሚያኖረኝ ፡ በደስታ
ሰው ፡ ሳያውቀኝ ፡ ቀድሞ ፡ ያወቀኝ
አትፍራ ፡ ልጄ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ ያለኝ
ውስጤን ፡ ልቤን ፡ የጣልኩበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ያኔ ፡ በመከራ ፡ የደገፈኝ
ሳለቅስ ፡ እምባዬን ፡ ያበሰልኝ
የቅኖች ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ አባቴ ፡ ነው (፪x)
ይሁን ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ይሆናል
ሃሳቡን ፡ ማን ፡ ይከለክላል
እንዴት ፡ ልርሳ ፡ መልካምነቱን
ልዘምር ፡ እንጂ ፡ ምህረቱን
ተስፋ ፡ ላጣ ፡ ተስፋ ፡ ነው ፡ ለምስኪኑ
ወዳጅ ፡ ላጣ ፡ ብቸኛ ፡ ነው ፡ ወገኑ
ላመስግነው ፡ እንጂ ፡ እኔ ፡ ልወድሰው
ኃይሌ ፡ ክብሬ ፡ ታሪኬም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ሰው ፡ ሳያውቀኝ ፡ ቀድሞ ፡ ያወቀኝ
አትፍራ ፡ ልጄ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ ያለኝ
ውስጤን ፡ ልቤን ፡ የጣልኩበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ያኔ ፡ በመከራ ፡ የደገፈኝ
ሳለቅስ ፡ እምባዬን ፡ ያበሰልኝ
የቅኖች ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ አባቴ ፡ ነው
ዮሴፍን ፡ ከእስር ፡ ቤት ፡ ያወጣ
ለሹመት ፡ ሽልማት ፡ ያበቃ
የዳንኤል ፡ አምላክ ፡ ተዐምረኛ
ከአንበሶኝ ፡ የሚያድን ፡ ከበላተኛ
አይገርምም ፡ ወይ ፡ ይሞታል ፡ የተባለው
ሕይወት ፡ ዘርቶ ፡ በግሩ ፡ ቆሞ ፡ አየነው
የቀመሰ ፡ ያውቀዋል ፡ የእርሱን ፡ ማዳን
የተነካ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ብርሃን
ጌታ ፡ በሕይወቴ ፡ ወዶ ፡ ያደረገውን
መጄም ፡ አልረሳውም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists