Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Selam lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Selam Vol. 5


ሰላም ፡ ነው ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ውሎ ፡ ማደር
መልካም ፡ አምላክ ፡ በእቅፉ ፡ ይዞኛል
አልሻም ፡ ምንም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለም
ፍቅሩ ፡ ከጨለማ ፡ ስቦ ፡ አውጥቶኛል
ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ
ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው (ኦሆሆሆ)
ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው
ሰላምን ፡ ይሿታል ፡ በወርቅ ፡ በብር ፡ ሊያገኟት
በዓልማዝ ፡ በዕንቁ ፡ አትመጣም ፡ ምን ፡ ያህል ፡ ቢያፈሱላት
ከእግዚአብሔር ፡ የታረቀ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የዘየደ
በአምላክ ፡ ሰላም ፡ ይጠግባል ፡ በመንገዱ ፡ የሄደ (፪x)
በፈቃዱ ፡ የሄደ (፪x)
ሰላም ፡ ነው ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ውሎ ፡ ማደር
መልካም ፡ አምላክ ፡ በእቅፉ ፡ ይዞኛል
አልሻም ፡ ምንም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለም
ፍቅሩ ፡ ከጨለማ ፡ ስቦ ፡ አውጥቶኛል
ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ
ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው (ኦሆሆሆ)
ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው
ሆድ ፡ በእንጀራ ፡ ቢሞላ ፡ ገላም ፡ ምርጡን ፡ ቢለብስ
የነፍስ ፡ ጐዶሎ ፡ አይሞላም ፡ ሰው ፡ ሁሉን ፡ ቢያግበሰብስ
ሰማያዊው ፡ ደስታ ፡ አምላክ ፡ ከላይ ፡ የላከው
ሰላም ፡ ማለት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ተሰፍሮ ፡ የማይለካው (፪x)
ሰው ፡ ዓለምን ፡ አትርፎ ፡ ውድ ፡ ነፍሱን ፡ ቢያዶላት
ከቶ ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል ፡ መጨረሻው ፡ ነው ፡ ጥፋት
ብሩክ ፡ ትሁን ፡ ያቺ ፡ ቀን ፡ ወንጌል ፡ የሰማሁባት
በክርስቶስ ፡ መስቀል ፡ ስራ ፡ ከአምላክ ፡ ጋር ፡ የታረቅኩባት (፪x)
ወንጌል ፡ የሰማሁባት ፡ አሄ ፡ ሰላም ፡ ያገኘሁባት
ሰላም ፡ ነው ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ውሎ ፡ ማደር
መልካም ፡ አምላክ ፡ በእቅፉ ፡ ይዞኛል
አልሻም ፡ ምንም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለም
ፍቅሩ ፡ ከጨለማ ፡ ስቦ ፡ አውጥቶኛል
ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ
ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው (ኦሆሆሆ)
ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists