Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Miheretun lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Selam Vol. 5


ጌታን ፡ ቸርነት ፡ ምህረቱን ፡ ሳስበው
መውጣቴ ፡ መግባቴ ፡ መኖሬ ፡ በእርሱ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የበዛው ፡ ፍቅር ፡ እጅግ ፡ ይገርመኛል
ሁሌ ፡ ሳታቋርጥ ፡ አመስግን ፡ ይለኛል
እጆቼን ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ ዘርግቼ
አመሰግነዋለሁ ፡ ስለተዋቡት ፡ ቀኖቼ
ኢየሱስ ፡ ሕያው ፡ አለት ፡ የኔ ፡ ጽኑ ፡ መሰረት
ምሥጋና ፡ ይብዛህ ፡ እንጂ ፡ ምሥጋና ፡ አይነስበት
አዝ: - ምህረቱን ፡ አይቼ ፡ ነው ፡ ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ነው
ዛሬ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ በፊቱ ፡ ቆሜ ፡ ምዘምረው (፪x)
በአባትነት ፡ ፍቅሩ ፡ ሁሌ ፡ እየመከረኝ
እግሬ ፡ ሲንሸራተት ፡ ይዞ ፡ እየደገፈኝ
በጸጋው ፡ ከልሎ ፡ እዚህ ፡ አድርሶኛል
እንዳመሰግነው ፡ ውስጤ ፡ ግድ ፡ ይለኛል
ልዘምር ፡ ለጌታዬ ፡ እርሱ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነው
እግሬን ፡ እመሰናከል ፡ ነፍሴ ፡ ከሞት ፡ ላዳነው
ልቅረብ ፡ በፊቱ ፡ ልስገድ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል
ሁልጊዜ ፡ ጠዋት ፡ አማታ ፡ ሳመልከው ፡ ደስ ፡ ይለኛል
አዝ: - ምህረቱን ፡ አይቼ ፡ ነው ፡ ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ነው
ዛሬ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ በፊቱ ፡ ቆሜ ፡ ምዘምረው (፪x)
ተአምራቱን ፡ ያየ ፡ ፍቅር ፡ የበዛለት
ድንቁ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሞገስ ፡ የሆነለት
ሳይቆጥብ ፡ ይናገር ፡ ያውራ ፡ የእርሱን ፡ ስራ
ተአምር ፡ እንደሚያድርግ ፡ ድንቅን ፡ እንደሚሰራ
ይናገር ፡ የቀመሰ ፡ ፍቅሩን ፡ መልካምነቱን
የሚያድን ፡ የሚታደግ ፡ ብሩህ ፡ አባት ፡ መሆኑን
አምላክ ፡ ነው ፡ የሚያስመካ ፡ እረዳት ፡ ድንቅ ፡ ሰሪ
ዘመኑ ፡ ቁጥር ፡ የለው ፡ ጌታ ፡ ዘለዓለም ፡ ነዋሪ
አዝ: - ምህረቱን ፡ አይቼ ፡ ነው ፡ ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ነው
ዛሬ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ በፊቱ ፡ ቆሜ ፡ ምዘምረው (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists