Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Anbesaw lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Selam Vol. 5


አዝ: - ከሁሉም ፡ የሚበልጥብኝ ፡ በማንም ፡ የማለውጠው
አንበሳው ፡ የጀግኖች ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ ግሩም ፡ እጁ ፡ ሰፊ ፡ ነው
ምንተስኖት ፡ ምን ፡ ያሳጣኛል
ቸርነቱን ፡ አብዝቶልኛል (፪x)
ያለፈው ፡ ታሪኬ ፡ አፍ ፡ አለው ፡ ያወራል
የጌታን ፡ ምህረት ፡ ፍቅር ፡ ይዘክራል
ያልተደረገልኝ ፡ ያልሆነ ፡ ምን ፡ አለ
የአምላኬ ፡ ምህረት ፡ በእኔ ፡ ገነነ
ያልተደረገልኝ ፡ ያልሆነ ፡ ምን ፡ አለ
የጌታ ፡ ምህረት ፡ በእኔ ፡ ገነነ
ይረዳል ፡ እኮ ፡ ከማንም ፡ በላይ
ተገርሜያለሁ ፡ ተአምራቱን ፡ ሳይ
ምስክሩ፡ ነኝ ፡ ሕያው ፡ ምልክቱ
ማዳኑን ፡ ያየሁ ፡ ሁሉን ፡ ቻይነቱን (፪x)
አዝ: - ከሁሉም ፡ የሚበልጥብኝ ፡ በማንም ፡ የማለውጠው
አንበሳው ፡ የጀግኖች ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ ግሩም ፡ እጁ ፡ ሰፊ ፡ ነው
ምንተስኖት ፡ ምን ፡ ያሳጣኛል
ቸርነቱን ፡ አብዝቶልኛል (፪x)
ምህረቱን ፡ እውነቱን ፡ ፍቅሩን ፡ አስብና
የከበረ ፡ ስሙን ፡ አሞጋግስና
ሳመልከው ፡ ሳከብረው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ልዘምር ፡ ድንቁን ፡ በምክሩ ፡ ስቦኛል
አምላክ ፡ ለክብሩ ፡ በስሜ ፡ ጠርቶኛል
ያስደስተኛል ፡ የጌታ ፡ መሆኔ
ምህረት ፡ አገኘሁ ፡ ዳንኩኝ ፡ ከኩነኔ (፪x)
አዝ: - ከሁሉም ፡ የሚበልጥብኝ ፡ በማንም ፡ የማለውጠው
አንበሳው ፡ የጀግኖች ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ ግሩም ፡ እጁ ፡ ሰፊ ፡ ነው
ምንተስኖት ፡ ምን ፡ ያሳጣኛል
ቸርነቱን ፡ አብዝቶልኛል (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists