Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Fiteret lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Selam Vol. 5


አዝ: - ፍጥረት ፡ የሚደገፍበት
እኔም ፡ ተስፋ ፡ ማደርግበት
ጌታ ፡ ነው ፡ እንከን ፡ የሌለበት
ልዘምር ፡ እስቲ ፡ ልቀኝለት
ለሕይወት ፡ ጥያቂ ፡ ለእንቆቅልሹ
ጌታ ፡ ነው ፡ ምላሽ ፡ አቻ ፡ የለሹ
ሁሉንም ፡ መልካም ፡ ያደርገውና
ያስገርመናል ፡ ድንቅ ፡ ይሰራና
ያድንና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ይባርክና (ኦሆሆሆሆ)
ሰው ፡ ያደርግና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ያቆምና (ኦሆሆሆሆ)
ይደግፍና
እየባረኩኝ ፡ እባርክሃለሁ
በሕይወትህ ፡ ድንቅን ፡ አደርጋለሁ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እንዳልከኝ
የኔ ፡ ጌታ ፡ ስንቱን ፡ አሳለፍከኝ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ አዳንከኝ ፡ ከጥፋት
ልገልጽ ፡ አልችል ፡ የውለታህን ፡ ብዛት
ድንቅን ፡ አይቻለሁ ፡ ድንቅን ፡ አይቻለሁ
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ ገና ፡ አመልክሃለሁ
ድንቅን ፡ አይቻለሁ ፡ ድንቅን ፡ አይቻለሁ
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ እገዛልሃለሁ
አዝ: - ፍጥረት ፡ የሚደገፍበት
እኔም ፡ ተስፋ ፡ ማደርግበት
ጌታ ፡ ነው ፡ እንከን ፡ የሌለበት
ልዘምር ፡ እስቲ ፡ ልቀኝለት
ለሕይወት ፡ ጥያቂ ፡ ለእንቆቅልሹ
ጌታ ፡ ነው ፡ ምላሽ ፡ አቻ ፡ የለሹ
ሁሉንም ፡ መልካም ፡ ያደርገውና
ያስገርመናል ፡ ድንቅ ፡ ይሰራና
ያድንና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ይባርክና (ኦሆሆሆሆ)
ሰው ፡ ያደርግና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ያቆምና (ኦሆሆሆሆ)
ይደግፍና
ቁሻሻውን ፡ ታሪኬን ፡ ለውጠህ
ሰው ፡ አደረከኝ ፡ ኢየሱስ ፡ በእኔ ፡ ከብረህ
ገና ፡ ህጻን ፡ ሳለሁ ፡ የተሸከምከኝ
በጉያህ ፡ ውስጥ ፡ እስካሁን ፡ አለሁኝ
አልተውህም ፡ አልጥልህም ፡ ያልከኝ
ኢየሱሴ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ድንቅን ፡ አይቻለሁ ፡ ድንቅን ፡ አይቻለሁ
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ ገና ፡ አመልክሃለሁ
ድንቅን ፡ አይቻለሁ ፡ ድንቅን ፡ አይቻለሁ
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ እገዛልሃለሁ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists