Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Yeredagnen lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yihonal


አዝ፦ ኦሆ ፡ የረዳኝን ፡ አመሰግናለሁ
በጉባኤው ፡ መሃል ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ
እኔንም ፡ ረድቶኛል ፡ በእውነት ፡ የምትሉ
እስኪ ፡ ዘምሩለት ፡ ለእርሱ ፡ እልል ፡ በሉ
እልል ፡ በሉ ፡ አሃሃ ፡ ዘምሩለት ፡ አሃሃ
ለድል ፡ ጌታ ፡ የድል ፡ መዝሙር ፡ ተቀኙለት
ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ኦሆሆ ፡ ሞገስ ፡ ለእርሱ ፡ ኦሆሆ
ለወደደን ፡ ላፈቀረን ፡ ለንጉሡ
እንደ ፡ እኔማ ፡ ቢሆን ፡ እንደበዛው ፡ ኃጢያቴ
በፊቱ ፡ ባልተገኘሁ ፡ ባይራራልኝ ፡ አባቴ
ምህረቱ ፡ ለእኔ ፡ በዛስ ፡ ቸርነት ፡ አደረገልኝ
አቤቱ ፡ መድሃኒቴ ፡ ይክበር ፡ ይመስገንልኝ (፬x)
አዝ፦ ኦሆ ፡ የረዳኝን ፡ አመሰግናለሁ
በጉባኤው ፡ መሃል ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ
እኔንም ፡ ረድቶኛል ፡ በእውነት ፡ የምትሉ
እስኪ ፡ ዘምሩለት ፡ ለእርሱ ፡ እልል ፡ በሉ
እልል ፡ በሉ ፡ አሃሃ ፡ ዘምሩለት ፡ አሃሃ
ለድል ፡ ጌታ ፡ የድል ፡ መዝሙር ፡ ተቀኙለት
ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ኦሆሆ ፡ ሞገስ ፡ ለእርሱ ፡ ኦሆሆ
ለወደደን ፡ ላፈቀረን ፡ ለንጉሡ
የውስጤን ፡ የልቤን ፡ ነግሬው ፡ ነበር
ፀሎቴን ፡ መልሶልኝ ፡ ጠላቴን ፡ አሳፈረ
ጉልበቴን ፡ አፀናልኝ ፡ ረዳኝ ፡ መድሃኒቴ
ድንቁን ፡ እዘምራለሁ
ያደረገውን ፡ በሕይወቴ ፡ የሰራውን ፡ በሕይወቴ (፫x)
አዝ፦ ኦሆ ፡ የረዳኝን ፡ አመሰግናለሁ
በጉባኤው ፡ መሃል ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ
እኔንም ፡ ረድቶኛል ፡ በእውነት ፡ የምትሉ
እስኪ ፡ ዘምሩለት ፡ ለእርሱ ፡ እልል ፡ በሉ
እልል ፡ በሉ ፡ አሃሃ ፡ ዘምሩለት ፡ አሃሃ
ለድል ፡ ጌታ ፡ የድል ፡ መዝሙር ፡ ተቀኙለት
ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ኦሆሆ ፡ ሞገስ ፡ ለእርሱ ፡ ኦሆሆ
ለወደደን ፡ ላፈቀረን ፡ ለንጉሡ
የታሰርኩበት ፡ ገመዴን ፡ በጥሶ
የጠላቶቼን ፡ ሰፈር ፡ መንደሩን ፡ አፈራርሶ
እንደ ፡ አንበሳ ፡ ደቦል ፡ ጀግንነት ፡ ሞልቶኛል
በጠላቶቼ ፡ ራስ ፡ ላይ ፡ አቁሞ ፡ ያዘምረኛል (፲፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists