Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Keberehen Lawraw lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yihonal


አዝ፦ እጅግ ፡ ያኮራኛል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ
አተረፍኩኝ ፡ እንጂ ፡ አልከሰርኩም ፡ እኔ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ እቅድ ፡ ነው
ወደ ፡ ፍቅርህ ፡ መንግሥት ፡ እንድፈልስ ፡ ያደረገው
ክብርህን ፡ ላውራው ፡ ልናገረው
በሰጠኸኝ ፡ ዜማ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነልኝን ፡ ላሰማ ፡ ምሥጋና
ኩራት ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ሳስበው
ለአንተ ፡ መለየቴ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይኸው ፡ ነው
ፍቅርህ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ በልጦብኛል
እንዳመልክህ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ ግድ ፡ ይለኛል
እንዴት ፡ ብዬ ፡ የሆዴን ፡ ልናገረው
ተመስገን ፡ ከማለት ፡ ሌላ ፡ ቃላት ፡ አጣሁ
እንዴት ፡ ብዬ ፡ የሆዴን ፡ ልናገረው
ምሥጋናዬ ፡ ምሥጋና ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላው
እንዴት ፡ ብዬ ፡ የሆዴን ፡ ልናገረው
ምሥጋናዬ ፡ ምሥጋና ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላው
አዝ፦ እጅግ ፡ ያኮራኛል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ
አተረፍኩኝ ፡ እንጂ ፡ አልከሰርኩም ፡ እኔ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ እቅድ ፡ ነው
ወደ ፡ ፍቅርህ ፡ መንግሥት ፡ እንድፈልስ ፡ ያደረገው
ክብርህን ፡ ላውራው ፡ ልናገረው
በሰጠኸኝ ፡ ዜማ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነልኝን ፡ ላሰማ ፡ ምሥጋና
ኩራት ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ሳስበው
ለአንተ ፡ መለየቴ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይኸው ፡ ነው
ዛሬማ ፡ ሰው ፡ አድርጐኛል ፡ ድንቅ ፡ ፍቅርህ
ሞገስ ፡ ሆኖኛል ፡ ጌታ ክቡር ፡ ሥምህ
በውዳሴ ፡ የተሞላ ፡ በምሥጋና
መዝሙር ፡ ይዘመርልህ ፡ የአንተ ፡ ነውና
በፈቃዴ ፡ ውዳሴን ፡ እጨምራለሁ
መድሃኒቴ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ አነግስሃለሁ (፪x)
አዝ፦ እጅግ ፡ ያኮራኛል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ
አተረፍኩኝ ፡ እንጂ ፡ አልከሰርኩም ፡ እኔ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ እቅድ ፡ ነው
ወደ ፡ ፍቅርህ ፡ መንግሥት ፡ እንድፈልስ ፡ ያደረገው
ክብርህን ፡ ላውራው ፡ ልናገረው
በሰጠኸኝ ፡ ዜማ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነልኝን ፡ላሰማ ፡ ምሥጋና
ኩራት ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ሳስበው
ለአንተ ፡ መለየቴ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይኸው ፡ ነው
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነ ፡ ያማረለት
ከአምላኩ ፡ ጋር ፡ መንገዱ ፡ የቀናለት
ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ አለ ፡ ቸር ፡ ጌታዬ
ክቡር፡ ሥምህን ፡ ልባርከው ፡ በዜማዬ
ክቡር ፡ ሥምህን ፡ እምላኬ ፡ ዛሬም ፡ ልባርከው
መድሃኒቴ ፡ እና ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ አነግስሃለሁ
አዝ፦ እጅግ ፡ ያኮራኛል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ
አተረፍኩኝ ፡ እንጂ ፡ አልከሰርኩም ፡ እኔ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ እቅድ ፡ ነው
ወደ ፡ ፍቅርህ ፡ መንግሥት ፡ እንድፈልስ ፡ ያደረገው
ክብርህን ፡ ላውራው ፡ ልናገረው
በሰጠኸኝ ፡ ዜማ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነልኝን ፡ ላሰማ ፡ ምሥጋና
ኩራት ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ሳስበው
ለአንተ ፡ መለየቴ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይኸው ፡ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists