Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Alamarerewem lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Yihonal


አዝ፦ ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ባይሞላ ፡ በዚህ ፡ አልመዝነውም
ከሁኔታዎች ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ማንም ፡ አይከሰውም (፪x)
አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ግሩም
የዘገየ ፡ ሲመስል ፡ ማንም ፡ አይቀድመውም
ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ ለእኔ ፡ ፀጋው ፡ ይበቃኛል
ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ ለእኔ ፡ ፍቅሩ ፡ ይበቃኛል
አዝ፦ ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ባይሞላ ፡ በዚህ ፡ አልመዝነውም
ከሁኔታዎች ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ማንም ፡ አይከሰውም (፪x)
ሁልጊዜ ፡ መንገዴን፡ በፊቱ
አጸናለሁ ፡ እግሬን ፡ በቤቱ
ለእኔስ ፡ ፍቅሩ ፡ ይበቃኛል
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከየት ፡ ይገኛል
እርሱ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ እድል ፡ ፈንታ
እርስቴ ፡ የሕይወቴ ፡ መከታ
ሁልጊዜ ፡ በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ከሁሉ ፡ ፍቅሩ ፡ በልጦብኛል
አዝ፦ ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ባይሞላ ፡ በዚህ ፡ አልመዝነውም
ከሁኔታዎች ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ማንም ፡ አይከሰውም (፪x)
አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ግሩም
የዘገየ ፡ ሲመስል ፡ ማንም ፡ አይቀድመውም
ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ ለእኔ ፡ ፀጋው ፡ ይበቃኛል
ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ ለእኔ ፡ ፍቅሩ ፡ ይበቃኛል
የሰው ፡ ፍላጐቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
የእግዚአብሔርን ፡ ፍቃድ ፡ እስኪለየው
በልቤ ፡ ብዙ ፡ ሃሳብ ፡ ይኖራል
የእግዚአብሔር ፡ የሆነው ፡ ይፀናል
ይፀናልኝ ፡ ለእኔስ ፡ የእርሱ ፡ ሃሳብ
ፈቃዱን፡ ለመጣስ ፡ አልሻም
ሃሳቤን ፡ የእርሱ ፡ ሃሳብ ፡ ይወረሰው
ሲገለጥ ፡ ሁሉም ፡ ለበጐ ፡ ነው
ተግቶ ፡ ለጠበቀው ፡ ጌታ ፡ ሲሰጥ ፡ ምላሹን
ለምን ፡ ተስፋ ፡ ልቁረጥ ፡ ሳልዘልቅ ፡ በትንሹ
መታገስ ፡ ጥሩ ፡ ነው ፡ ብዙ ፡ ድንቅን ፡ ያሳያል
ፀንቶ ፡ የጠበቀ ፡ መልካም ፡ ፍሬ ፡ ይበላል
ከሁሉ ፡ የበለጠ ፡ ክብሩን ፡ አይቻለሁ
ወደር ፡ የለሽ ፡ ፍቅሩን ፡ ምሕረት ፡ አግኝቻለሁ
በትልቅ ፡ ትንሹ ፡ እንዴት ፡ አማርራለሁ
የተደረገልኝ ፡ እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists