Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - ሞኝነት ሆኖ አይደለም lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: ሞኝነት ሆኖ አይደለም


ሞኝነት ሆኖ አይደለም ፍቅሩን ቀምሼ ነው
ና ሲለኝ የተከተልኩት ነፍሴ ተማርካ ነው
ጠቢባን ያላዩት ዕውቀት ለእኔ ተገልጦ ነው
የጌታን የማዳን ሚስጢር ነፍሴ ተረድታው ነው
ከወርቅ ከዕንቁ በልጦብኝ ነው
ከማንም በላይ ተመችቶኝ ነው
የቱ ነው ታዲያ ሞኝነቴ
ለእኔ ጥበብ ነው ጌታን ማወቄ
ኤሄሄ
አምላኬን ማወቄ
አምላኬን ማወቄ
አሃሃ
አምላኬን ማወቄ
እኔስ መድኃኒቴን ተስፋ አደርገዋለሁ
እኔስ ኢየሱሴን ተስፋ አደርገዋለሁ
ቢጐድልም ቢሞላው በእርሱ እታመናለሁ
እርሱ አይለየኝም ይህንን አውቃለሁ
ድንቁን አይቻለሁ በሕይወት ዘመኔ
ከኢየሱሴ በቀር ጌታ አላውቅም እኔ
ሞት ያላሸነፈው አምላክ እርሱ ብቻ
ዘመን የማይሽረው ነው የሌለው አቻ
አምላኬን ማወቄ
አሃሃ
አምላኬን ማወቄ
ምስክር ነኝ እኔ ኢየሱስ ያድናል
ከኃጢአት እሥራት ከደዌም ይፈታል
ሰላሙ ብዙ ነው እረፍትን ይሰጣል
ተስፋ ለቆረጡት ተስፋቸውን ያድሳል
ኃያላን ነን ያሉ በእርሱ ላይ ቢነሱ
ወድቀው ተረሱ እንጂ ለአፍታም አልታወሱ
የእኛ ግን ኢየሱስ በልባችን ያለው
ፍቅሩ የማይጠገብ ዘለዓለማዊ ነው
ዓይኔ በርቶልኛል ጌታን አውቄያለሁ
ከዚህ በላይ የለም ምን እፈልጋለሁ
የዘለዓለም ሕይወት በነጻ አግኝቻለሁ
በእርሱ ተመርጬ በፊቱ አዜማለሁ
እዘምራለሁኝ አልታክትም ሁሌ
ስለ እርሱ ዝም ልል ከቶ አልችልም እኔ
የማዳኑን ወንጌል በዜማ አወራለሁ
ኢየሱስ ያድናል እመሰክራለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists