Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - ምን ልበል lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: ሞኝነት ሆኖ አይደለም


እኔ ምን ልበል ስንቱን አወራለሁ
የቱንስ አውርቼ የቱን እተዋለሁ
ያደርገልኝን ቢቆጠር በየተራ
ከአይምሮየ በላይ የሱ ሥራ
እኔማ ምን ልበል ስንቱን ላውራ
ከአይምሮየ በላይ የሱ ሥራ
ክብር የእግዚአብሔር ነው
ክብር የኢየሱስ ነው
ተመስገን የምለው ካሳ ሆኖ አይደለም
የጌታን ውለታ የሚክሠው የለም
ክበርም የምለው ስለሚገባው ነው
ለውለታው ምላሽ ሊሠጥ የሚችል ማን ነው
እኔማ ምን ልበል ስንቱን ላውራ
ከአይምሮየ በላይ የሱ ሥራ
አምላኬ ነህ ጌታየ ወዳጄ እንከን የሌለህ
ፍቅርህ ለኔ በቂ ነው ሁሌ ታጠግበኛለህ
አምላኬ ነህ ኢየሱሴየ ወዳጄ እንከን የሌለህ
ፍቅርህ ለኔ በቂ ነው ሁሌ ታጠግበኛለህ
ስለዚህ ስለዚህ በፍፁም ልቤ ጌታየ እወድሃለሁ
ዘመኔን ዘመኔን እያከበርኩ ለመኖር ወስኛለሁ
ስለዚህ ስለዚህ በፍፁም ልቤ ጌታየ እወድሃለሁ
ዘመኔን ዘመኔን እያከበርኩ ለመኖር ወስኛለሁ
ከእሱ የሆነውን ለእሱ አቀርባለሁ
እኔማ ምን አለኝ ምን እሰጠዋለሁ
እንዲሁ በፀጋ ፊቱ አቁሞኛል
ስለፈቀደልኝ አመስግን ብሎኛል
ስለፈቀደልኝ አሀሀ አመስግን ብሎኛል
ስለፈቀደልኝ አሀሀ አክብረኝ ብሎኛል
አምላኬ ነህ ጌታየ ወዳጄ እንከን የሌለህ
ፍቅርህ ለኔ በቂ ነው ሁሌ ታጠግበኛለህ
አምላኬ ነህ ኢየሱሴየ ወዳጄ እንከን የሌለህ
ፍቅርህ ለኔ በቂ ነው ሁሌ ታጠግበኛለህ
ስለዚህ ስለዚህ በፍፁም ልቤ ጌታየ እወድሃለሁ
ዘመኔን ዘመኔን እያከበርኩ ለመኖር ወስኛለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists