Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Mesmamat lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Anbesa


ሀሳቤ ፡ የልቤ ፡ ባይሞላ
ያቀድኩት ፡ ነገር ፡ ባይሰካ
ላመስግን ፡ ልተው ፡ ማማረሬን
ያልከው ፡ ይሁን ፡ ጌታ
ያ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ለእኔ
አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል
መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል
ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም
በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x)
ችግሬ ፡ ረሃቤ ፡ ቢፀናም
ቁስሌ ፡ ባይደርቅ ፡ ፈውሴ ፡ ቢዘገይ
ከፈቀድከው ፡ ይሁን ፡ ማለት
አስተምረኝ ፡ ጌታዬ ፡ ትግስትን
አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል
መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል
ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም
በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x)
ጌታ ፡ ነህ ፡ ብትገል ፡ ብታድንም
መከራከር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ኣይበጅም
ክፉ ፡ አይደለህም ፡ ጨካኝ
ለአላማህ ፡ ጌታ: ነው ፡ ጌታ: የምትመራኝ
አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል
መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል
ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም
በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x)
አንተ ፡ ያልከው ፡ ይሻለኛል
የእራሴማ ፡ መቼ ፡ ያዋጣኛል
ትርፉ ፡ መመረር ፡ መቁሰል ፡ ነው
ለአንተ ፡ ሀሳብ ፡ ጌታ ፡ መገዛት ፡ ጥሩ ፡ ነው
አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል
መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል
ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም
በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x)
በሥራው ፡ ሁልጊዜ ፡ ጻድቅ ፡ ነህ
ተሳስተህስ ፡ መቼ ፡ ታውቃለህ
ሀሳቤን ፡ በሀሳብህ ፡ ጠቅልለው
ምኞቴንም ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ ቃልህ ፡ አርገው
አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መስማማት ፡ ይሻላል
መማረር ፡ ማኩረፍ ፡ ምን ፡ ያዋጣል
ፈቃድህ ፡ ይሁን ፡ ማለት ፡ መልካም
በጊዜው ፡ ነገር ፡ ውብ ፡ ይሆናል (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists