Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Kewededkew lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Anbesa


ከወደድከው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ጌታ ፡ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታዬ ፡ አልሰለችም (፪x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ከሚሉት ፡ እልፍ ፡ አላፍት ፡ መላዕክቶች
እኔንም ፡ ከደመርከኝ ፡ ከቤትህ ፡ ተቀኚዎች
መስዋዕቴን ፡ ከወደድከው ፡ ደስ ፡ ከተሰኸኘህበት
ይኸው ፡ ዝማሬ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተው ፡ ከፍ ፡ በልበት
ከወደድከው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ጌታ ፡ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታዬ ፡ አልሰለችም (፪x)
ጠቢባን ፡ አዋቂዎች ፡ በምድር ፡ ሞልተው ፡ እያሉ
ጥሪ ፡ አልደረሳቸውም ፡ ለዚህ ፡ ክብር ፡ አልታደሉም
ታላላቆቹን ፡ ንቀህ ፡ ምስኪኑን ፡ ታከብረዋለህ
ኧረ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ፊት ፡ አይተህ ፡ መቼ ፡ ታደላለህ
ከወደድከው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ጌታ ፡ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታዬ ፡ አልሰለችም (፪x)
ጠዋትም ፡ ማታም ፡ በአፌም ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ
የተቀደሰውን ፡ ሥምህን ፡ አከብራለሁ
ብቁ ፡ ሆኜ ፡ አይደለም ፡ ለዚህ ፡ የተገባሁኝ
ጌታ ፡ በምህረትህ ፡ ነው ፡ አንተው ፡ ይሁን ፡ ስላልከኝ
ከወደድከው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ጌታ ፡ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታዬ ፡ አልሰለችም (፪x)
በህፃናት ፡ አፍም ፡ ምሥጋናን ፡ ታኖራለህ
የምስኪኑን ፡ አንደበት ፡ ዝማሬን ፡ ትሞላለህ
ይሁን ፡ አንተ ፡ ከፈቀድከው ፡ ይህንን ፡ ከወደድከው
እኔማ ፡ አይሰለቸኝም ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ አዜማለሁ
ከወደድከው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ጌታ ፡ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታዬ ፡ አልሰለችም (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists