Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Yante Fiker Gen lyrics

Artist: Daniel Amdemichael

album: Anbesa


አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ
መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ
የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ
ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ
ኢየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ ተሰጥቻለሁ
ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ (፪x)
ብዙ ፡ የከበሩ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ሞልተው
ታላቅ ፡ ነኝ ፡ ባዩን ፡ ልታሳፍረው
እኔን ፡ መረጥከኝ ፡ ዓሣ ፡ አጥማጁን ፡ ሰው
ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ ፡ ፍቅርህ
ሀብታም: ደሀ ፡ አይል ፡ አመራረጥህ
ለእኔም ፡ ደረሰኝ ፡ ድንቅ ፡ ማዳንህ
አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ
መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ
የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ
ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ
ኢየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ ተሰጥቻለሁ
ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ
መች: ያልቃል፡ ጥረቴ ፡ ለዚህ ፡ ሥጋዬ
ቀን ፡ ከሌት፡ ስደክም ፡ መረቤን ፡ ጥዬ
ምንም ፡ ላላገኝ ፡ በድካም ፡ ዝዬ
አንተ ፡ ግን ፡ መጥተህ ፡ ተዓምርን ፡ ሰራህ
መላው ፡ ሕይወቴን ፡ መገረም ፡ ሞላ
ሥሜን ፡ ተግባሬን ፡ ኑሮዬን ፡ ቀየርክ
አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ
መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ
የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ
ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ
ኢየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ ተሰጥቻለሁ
ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ
ከኋላዬ ፡ ና ፡ ወድጄሃልሁ
ለማዳን ፡ ሥራ ፡ መርጬሃልሁ
ሰዎችን ፡ አጥማጅ ፡ አደርግሃልሁ
ኣለኝ፡ ጌታዬ ፡ እኔም ፡ ተረታሁ
ከልብ ፡ ወደድኩህ ፡ ሕይወቴን ፡ ሰጠሁ
እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ አመልክሃለሁ
አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ
መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ
የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ
ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ
ኢየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ ተሰጥቻለሁ
ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ
የዋህነትህ፡ ትህትናህ ፡ ነው: የሳበኝ
በኃይል ፡ በጉልበት ፡ አላስገደድከኝ
ድንቅ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው ፡ ያንበረከከኝ
ልከተል ፡ ወሰንኩ ፡ ከልብ ፡ ጌታዬ
በነገር ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ ታምኜ
መረብ ፡ ታንኳዬን ፡ ሁሉንም ፡ ጥዬ
አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ
መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ
የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ
ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ
ኢየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ ተሰጥቻለሁ
ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists