Kishore Kumar Hits

Mesfin Gutu - Alisham lyrics

Artist: Mesfin Gutu

album: Negen Ayalehu, Vol.7


በረሃብ ፡ ቀጠና ፡ አይደለሁም ፡ እኔ
ልምላሜ ፡ ረግፎ ፡ አልገደለኝ ፡ ጠኔ
በአረንጓዴው ፡ ገነት ፡ ምንጭ ፡ በሚፈልቅበት
እንድኖር ፡ ተፈርዷል ፡ በኢየሱስ ፡ ዳኝነት
አልሻም ፡ ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም
በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም
አልሻም ፡ ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም
በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም
አልፈልግም ፡ ዳግም
አልፈልግም ፡ ዳግም (እምቢ)

ለምንድን ፡ ነው ፡ አሉኝ ፡ ክርስትያን ፡ የሆንከው
ሁልጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ምትለው
እስቲ ፡ ልንገራችሁ ፡ ይህንን ፡ ሚስጥር
ስበቱ ፡ አይሎ ፡ ነው ፡ የመስቀሉ ፡ ፍቅር
አልሻም ፡ ከሱ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም
በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም
አልሻም ፡ ከሱ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም
በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም
አልፈልግም ፡ ዳግም
አልፈልግም ፡ ዳግም (እምቢ)

ነፍሴ ፡ አዋጅ ፡ ሰምታ ፡ የሞትን ፡ ቀጠሮ
ፍጥረት ፡ ሲያወራ ፡ የሽንፈት ፡ እሮሮ
ሕይወት ፡ ያበዛልኝ ፡ ማነው ፡ ከተባለ
አዳኙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ በዙፋኑ ፡ ያለ
አልሻም ፡ ከእርሱ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም
በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም
አልሻም ፡ ከእርሱ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም
በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም
አልፈልግም ፡ ዳግም
አልፈልግም ፡ ዳግም (እምቢ)

እንግዲህ ፡ በኢየሱስ ፡ ተደላድያለሁ
ዓለም ፡ የማይሰጠውን ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ
ታዲያ ፡ ለምን ፡ ልሩጥ ፡ ለምን ፡ ልቅበዝበዝ
እስቲ ፡ በኢየሱስ ፡ ላይ ፡ እርፍ ፡ ልበል
እርፍ ፡ ድግፍ ጥግት ፡ ጥግት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists