Kishore Kumar Hits

Ephrem Alemu - Ye Hiwote Kale Aleh lyrics

Artist: Ephrem Alemu

album: Yenefse Mamlecha, Vol. 1


ያምላኬ ፡ ጉዳይ ፡ ከበደብኝ
ቅጥሩ ፡ ፈርሶ ፡ ስላየሁኝ
ልቤን ፡ ላስታመው ፡ ደግሞ ፡ ምግብ ፡ አልበላ
ቅጥሩ ፡ ታድሶ ፡ ካላየሁማ
ኧኸ ፡ ጦቢያው ፡ ሰምበላት
ኧኸ ፡ ውረድ ፡ ሲሉኝ
ቅጥር ፡ ልሰራ ፡ ሄጃለሁኝ (፪x)
ና ፡ ውረድ ፡ ሲሉኝ (፫x)
ስፍራው ፡ ተመችቶኝ ፡ እዛው ፡ ቀረሁኝ
አልወርድም ፡ አልወርድም ፡ ከተራራው ፡ ላይ
የእግዚአብሔርን ፡ ክብር ፡ በዓይኖቼ ፡ እስከማይ
አልዛቤል ፡ ምድሩን ፡ ሃገሩን ፡ ገዝታ
ምን ፡ ሰላም ፡ አለ ፡ ለእኛ ፡ መኝታ
እረፍት ፡ የለኝም ፡ ለሽፋሽፍቴ
እስካያት ፡ ድረስ ፡ ወድቃ ፡ ከፊቴ
ኧኸ ፡ ውሻ ፡ ሲበላት
ኧኸ ፡ በዓይኔ ፡ አያለሁ
የትናገረኝ ፡ ጌታ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፪x)
ና ፡ ውረድ ፡ ሲሉኝ (፫x)
ስፍራው ፡ ተመችቶኝ ፡ እዛው ፡ ቀረሁኝ
አልወርድም ፡ አልወርድም ፡ ተራራው ፡ ላይ
የእግዚአብሔርን ፡ ክብር ፡ በዓይኖቼ ፡ እስከማይ
ቤቱ ፡ በሸቀጥ ፡ ነጋዴ ፡ ሞልቶ
አጠራው ፡ ጌታ ፡ ጅራፍን ፡ ሰርቶ
ሁሉም ፡ ይሰግዳል ፡ ለአብ ፡ ክብር
ቤቱ ፡ ሲጠራ ፡ የእግዚአብሔር
ኧኸ ፡ የቤቱ ፡ ቅናት
ኧኸ ፡ እኔን ፡ በልቶኛል
ቤቱ ፡ ሲጠራ ፡ በዓይኔ ፡ ያሳየናል (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists