Kishore Kumar Hits

Dagi Tilahun - Yilal Gena lyrics

Artist: Dagi Tilahun

album: Geta Ale Kegonea, Vol. 2


አምላኬ ፡ እድሌ ፡ ፈንታዬ
ያለመለምከው ፡ ተስፋዬን
መሞት ፡ ሲገባኝ ፡ ኩነኔ
እኔስ ፡ ገረመኝ ፡ መዳኔ
አምላኬ ፡ እድሌ ፡ ፈንታዬ
ያለመለምከው ፡ ተስፋዬን
መሞት ፡ ሲገባኝ ፡ ኩነኔ
እኔስ ፡ ገረመኝ ፡ መዳኔ
ገረመኝ ፡ መዳኔ ፡ መዳኔ ፡ ገረመኝ ፡ መዳኔ
ገረመኝ ፡ መዳኔ ፡ መዳኔ ፡ ገረመኝ ፡ መዳኔ
ውለታ ፡ ያለበት ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል
እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል
ፍቅሩን ፡ የቀመሰ ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል
እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል
ያደረግልኝን ፡ ጌታ ፡ ይሆነልኝን
አስቤው ፡ ያን ፡ ዘመን ፡ በርሱ ፡ ያለፍኩትን
ክበር ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ
ንገሥ ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ
ክበር ፡ ልበለው ፡ አከብረዋለሁኝ
ንገሥ ፡ ልበለው ፡ አነግሰዋለሁኝ
ቅጥቅጥ ፡ ሸንበቆ ፡ አትሰብርም
የወደቀ ፡ አይተህ ፡ አታልፍም
አልቀረሁ ፡ ምስኪን ፡ ተብዬ
ባንተ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ ጌታዬ
ቅጥቅጥ ፡ ሸንበቆ ፡ አትሰብርም
የወደቀ ፡ አይተህ ፡ አታልፍም
አልቀረሁ ፡ ምስኪን ፡ ተብዬ
ባንተ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ ጌታዬ
ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ ጌታዬ
ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ ጌታዬ
ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ ጌታዬ
ቀራኒዮን ፡ ያሰበ ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል
እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል
ከሞት ፡ ያመለጠ ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል
እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል
ያደረግልኝን ፡ ጌታ ፡ ይሆነልኝን
አስቤው ፡ ያን ፡ ዘመን ፡ በርሱ ፡ ያለፍኩትን
ክበር ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ
ንገሥ ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ
ክበር ፡ ልበለው ፡ አከብረዋለሁኝ
ንገሥ ፡ ልበለው ፡ አነግሰዋለሁኝ
ቤቴ ፡ በክብሩ ፡ ተሞላና
እኔም ፡ ወግ ፡ አየሁ ፡ እንደገና
ቤቴ ፡ በክብሩ ፡ ተሞላና
እኔም ፡ ወግ ፡ አየሁ ፡ እንደገና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ
ሳልሰለች ፡ በደስታ ፡ ልዘምር ፡ ለጌታ
ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ ምነው ፡ በሆንኩለት
ምነው ፡ በሆንኩለት ምነው ፡ በሆንኩለት
ሕይወቴ ፡ ያማረው ፡ እርሱን ፡ ያገኘሁ ፡ እለት
እርሱን ፡ ያገኘሁ ፡ እለት ፡ እርሱን ፡ ያገኘሁ ፡ እለት
አንደበቴን ፡ ልክፈት ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና
በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና
በቅቶኝ ፡ አልቀመጥ ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና
ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና
ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና
ይላል ፡ ገና ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና
ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና
ይላል ፡ ገና ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና
ይላል ፡ ገና ፡ ምስጋና
ይላል ፡ ገና ፡ ገናና
ይላል ፡ ገና ፡ አምልኮ
ይላል ፡ ገና ፡ ዝማሬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists