Kishore Kumar Hits

Dagi Tilahun - Syned Yisemagnal lyrics

Artist: Dagi Tilahun

album: Geta Ale Kegonea, Vol. 2


የፍቅርህ ፡ ልክ ፡ የፍቅርህ ፡ ገደብ
በዝቶብኝ ፡ እኔስ ፡ ለማሰብ
አይጠፋም ፡ ሥምህ ፡ ከአፌ
አይወጣም ፡ ፍቅርህ ፡ ከልቤ (፪x)
ቀስቃሽ ፡ አልፈልግም ፡ ሳመልክህ
መች ፡ በረደ ፡ ውስጤ ፡ ያ ፡ ፍቅርህ
ሲነድ ፡ ይሰማኛል ፡ በላዬ
እወድሃለሁኝ ፡ ጌታዬ (፪x)
ኢየሱሴ ፡ ለኔ ፡ ምትክ ፡ የለህ
ልቤም ፡ ሌላ ፡ አይሻ ፡ አንተ ፡ እያለህ
ከፍ ፡ የምታደርግ ፡ በአንተ ፡ ጊዜ
ዙፋንህ ፡ ሥር ፡ ልስገድ ፡ ሁልጊዜ
ተባረካ ፡ ጌታዬ ፡ ተባርክ
ተባረካ ፡ አምላኬ ፡ ተባረክ (፪x)
ምን ፡ ይከፈልሃል ፡ ጌታዬ ፡ (አሃሃ) ፡ ጌታዬ
ሁሉ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ (አሃሃ) ፡ አምላኬ
ምሥጋናና ፡ አምልኮ ፡ አምልኮ ፡ (አሃሃ) ፡ ምሥጋና
መቼ ፡ ይበዛብሃል ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ (አሃሃ) ፡ ገናና
ተመስገንልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገንልኝ
ከሕያዋን ፡ ጋር ፡ ሥምህን ፡ አከብራለሁኝ
ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክልኝ
ከሚወዱህ ፡ ጋር ፡ ሥምህን ፡ አከብራለሁኝ
እንዳለፈ ፡ ውሃ ፡ መከራዬን
ረስቼዋለሁ ፡ ሳየው ፡ ጌታን
እኔስ ፡ አልሰጋም ፡ ከእንግዲህስ ፡ ብዬ
እዚህ ፡ ያደረስኝ ፡ አለ ፡ ጌታዬ
አለ ፡ ጌታዬ ፡ (አለ) (፰x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists