Kishore Kumar Hits

Yosef kassa - Teregagtual lyrics

Artist: Yosef kassa

album: Zmtaw


አንዴ ፡ በፍቅሩ ፡ ልቤ ፡ ተነክቶ
ሌላውን ፡ ናቀው ፡ በኢየሱስ ፡ ረክቶ
በነገረኝ ፡ ቃል ፡ በእርሱ ፡ ጸንቼ
ዘና ፡ ብያለሁ ፡ ጌታን ፡ ሰምቼ
ተረጋግቷል ፡ ልቤ ፡ ተረጋግቷል
ተረጋግቷል ፡ ልቤ ፡ ተረጋግቷል
በአምላኩ ፡ ታምኖ ፡ እፎይ ፡ አለ
ከአንተ ፡ ድምጽ ፡ ውጪ ፡ አልሰማ ፡ አለ
ኢየሱስን ፡ ይዞ ፡ ቃሉን ፡ ተመርኩዞ
በትከሻው ፡ መሃል ፡ ተንተርሶ
ኢየሱስን ፡ ይዞ ፡ ቃሉን ፡ ተመርኩዞ
በትከሻው ፡ መሃል ፡ ተንተርሶ
ልቤም ፡ አይፈራም ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ
አይደነብርም ፡ ጠላቱን ፡ ሰምቶ
እነድ ፡ አንበሳ ፡ ነው ፡ ውስጠ ፡ ድፍረቴ
አንዴ ፡ አትርፌያለሁ ፡ በማንነቴ
በውይኑ ፡ ሃረግ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ
ቢሆንም ፡ ባይሆን ፡ አያስጨንቀኝ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ዓይናወጥም ፡ ከቶ ፡ እምነቴ
የሰላም ፡ አምላክ ፡ ገብቷል ፡ ከቤቴ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ይህን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ጀግና ፡ ሚሉት
አይደነብርም ፡ በሚነግሩት
በሰልፍ ፡ መሃል ፡ በምጥ ፡ ተይዞ
ይደረድራል ፡ በገናን ፡ ይዞ
ክበር ፡ እያለ ፡ ንገሥ ፡ እያለ
ክበር ፡ እያለ ፡ ንገሥ ፡ እያለ
ተረጋግቷል ፡ ልቤ ፡ ተረጋግቷል
ተረጋግቷል ፡ ልቤ ፡ ተረጋግቷል
በአምላኩ ፡ ታምኖ ፡ እፎይ ፡ አለ
ከአንተ ፡ ድምጽ ፡ ውጪ ፡ አልሰማ ፡ አለ
ኢየሱስን ፡ ይዞ ፡ ቃሉን ፡ ተመርኩዞ
በትከሻው ፡ መሃል ፡ ተንተርሶ
ኢየሱስን ፡ ይዞ ፡ ቃሉን ፡ ተመርኩዞ
በትከሻው ፡ መሃል ፡ ተንተርሶ
ጠላት ፡ ሁኔታን ፡ እያሳየኝ
ልቤ ፡ እንዲከፋ ፡ ሲጠብቀኝ
ይናፍቀዋል ፡ እንባ ፡ ከዓይኖቼ
ምሥጋና ፡ ሞልቷል ፡ ከከንፈሮቼ
በውይኑ ፡ ሃረግ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ
ቢሆንም ፡ ባይሆን ፡ አያስጨንቀኝ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ዓይናወጥም ፡ ከቶ ፡ እምነቴ
የሰላም ፡ አምላክ ፡ ገብቷል ፡ ከቤቴ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ይህን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ጀግና ፡ ሚሉት
አይደነብርም ፡ በሚነግሩት
በሰልፍ ፡ መሃል ፡ በምጥ ፡ ተይዞ
ይደረድራል ፡ በገናን ፡ ይዞ
ክበር ፡ እያለ ፡ ንገሥ ፡ እያለ
ክበር ፡ እያለ ፡ ንገሥ ፡ እያለ
የእምነት ፡ አባቶቼ ፡ እንዲህ ፡ መከሩኝ
ሁል ፡ ጊዜ ፡ በጌታ ፡ ተደሰት ፡ አሉኝ
ውህኒ ፡ ቢከቷቸው ፡ የማይመች ፡ ቦታ
መዘመር ፡ ቀጠሉ ፡ ውስጣቸው ፡ ነው ፡ ደስታ
ቢሆንም ፡ ባይሆን ፡ አመስግኑ
መልካም ፡ እንዲሆን ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ
አታጉረምርሙ ፡ አመስግኑ
አምላክ ፡ አትሙ ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ
ቅዱሳን ፡ ሁሉ
ለእርሱ ፡ ዘምሩ
አንሱ ፡ በገና
አምጡ ፡ ምሥጋና
ቢሆንም ፡ ባይሆን ፡ አመስግኑ
መልካም ፡ እንዲሆን ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ
አታጉረምርሙ ፡ አመስግኑ
አምላክ ፡ አትሙ ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ
ቢሆንም ፡ ባይሆን ፡ አመስግኑ
መልካም ፡ እንዲሆን ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ
አታጉረምርሙ ፡ አመስግኑ
አምላክ ፡ አትሙ ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ ፡ አመስግኑ
ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists