Kishore Kumar Hits

Yosef kassa - Kenoruma lyrics

Artist: Yosef kassa

album: Zmtaw


ንፋሱ ፡ ነፈሰና ፡ አለፈ
ወጀቡም ፡ ጸጥ ፡ አለ ፡ አለፈ
መንገዴን ፡ ዞር ፡ በዬ ፡ ሳየው
ይህ ፡ ሁሉ ፡ ለመልካም ፡ የሆነው
ስላለ ፡ ጌታ ፡ አጠገቤ
ስላለ ፡ አባ ፡ አጠገቤ
ከኖሩማ ፡ ኑሮ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
በችግር ፡ ቢሆን ፡ በመከራ
ከተያዘም ፡ እጄ ፡ በአንተ ፡ እጅ
ሕይወቴ ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ የሚመች
ስሄድ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ በሕይወት ፡ መንገድ
ምንም ፡ ነገር ፡ አይሆን ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ፈቃድ
አያስጨንቀኝም ፡ ነገ ፡ የሚሆነው
የነፍሴ ፡ ፍጻሜ ፡ በእጅህ ፡ ነው
የእኔ ፡ ነገር ፡ ሰው ፡ ይማይዘጋው ፡ ሰው ፡ የማይከፍተው
ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
የእኔ ፡ ነገር ፡ መጀመሪያዬ ፡ መጨረሻዬ
በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ
ከኖሩማ ፡ ኑሮ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
በችግር ፡ ቢሆን ፡ በመከራ
ከተያዘም ፡ እጄ ፡ በአንተ ፡ እጅ
ሕይወቴ ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ የሚመች
ሲጸልይ ፡ ዳናኤል ፡ አንተን ፡ ስለጠራ
ጉድ ፡ ጓድ ፡ ውስጥ ፡ ከተቱት ፡ በአንበሳ ፡ እንዲበላ
ይንከባከቡታል ፡ እንኳን ፡ ሊበሉት
ችግር ፡ ይቀየራል ፡ በምቾት
የእኔ ፡ ነገር ፡ ሰው ፡ ይማይዘጋው ፡ ሰው ፡ የማይከፍተው
ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
የእኔ ፡ ነገር ፡ መጀመሪያዬ ፡ መጨረሻዬ
በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ
ቆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ከአንተ ፡ የራቀ ፡ የተሰወረብህ
እኮ ፡ ምን ፡ አለ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሁሉን ፡ የምታውቅ
ቆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ድንገት ፡ ተገልጦ ፡ የሚያስደነግጥህ
እኮ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሰማይ ፡ ምድሩን ፡ ሁሉን ፡ በእጅህ ፡ ይዘህ
መላ ፡ ሕይወቴ ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ
እድሜ ፡ ዘመኔ ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ
ነገዬም ፡ ቢሆን ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ
እስትንፋሴ ፡ እንኳን ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists