Kishore Kumar Hits

Yosef kassa - Biberama lyrics

Artist: Yosef kassa

album: Zmtaw


በመንገዴ ፡ ስሄድ ፡ ስራመድ ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና
እግሮቼ ፡ በቤትህ ፡ ጸንተው ፡ ዓይኔ ፡ ግን ፡ ሳይበራ
የሚሄደው ፡ የሚመጣው ፡ ሲያዳክመው ፡ ፡ ልቤን
የቆምኩኝ ፡ ያለሁኝ ፡ መስሎኝ ፡ እያንገዳገደኝ
አልገባኝም ፡ ነበር ፡ የልቦና ፡ ዓይኔ ፡ ታውሮ
ምድር ፡ ምድር ፡ አለ ፡ የከበረውን ፡ ሰማይን ፡ ጥሎ
ቃልህን ፡ ስሰማ ፡ ልቤ ፡ ተደስቶ
ለጊዜው ፡ ነበረ ፡ በስሜት ፡ ተገፍቶ
ነፋስና ፡ ጐርፉ ፡ ሊፈትነኝ ፡ መጣ
ይታወቀኝ ፡ ጀመር ፡ ከመንገድ ፡ ስወጣ
ቢበራማ ፡ በቃልህ ፡ ቢጸና ፡ ዓይኔ ፡ ቢበራ
ቢበራማ ፡ ጸንቶ ፡ ይቆም ፡ ነበር ፡ ፍሬ ፡ እያፈራ
ቢበራማ ፡ ቅርንጫፍ ፡ ከግንዱ ፡ ከተጣበቀ
ቢበራማ ፡ ያስታውቃል ፡ መልኩ ፡ አንተን ፡ ያወቀ
ዓይኖቼን ፡ አብራ ፡ ክፈት ፡ ዓይኔን
እነደ ፡ እኔ ፡ ሳይሆን ፡ እንዳንተ ፡ እንዳይ
በመንገዴ ፡ ስሄድ ፡ ስራመድ ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና
እግሮቼ ፡ በቤትህ ፡ ጸንተው ፡ ዓይኔ ፡ ግን ፡ ሳይበራ
የሚሄደው ፡ የሚመጣው ፡ ሲያዳክመው ፡ ፡ ልቤን
የቆምኩኝ ፡ ያለሁኝ ፡ መስሎኝ ፡ እያንገዳገደኝ
አልገባኝም ፡ ነበር ፡ የልቦና ፡ ዓይኔ ፡ ታውሮ
ምድር ፡ ምድር ፡ አለ ፡ የከበረውን ፡ ሰማይን ፡ ጥሎ
ሲዘነጋ ፡ ለቤ ፡ የሰማዩን ፡ ቤቱን
በዚህ ፡ ምድር ፡ሲኖር ፡ እንግዳ ፡ መሆኑን
አይጐመጅም ፡ ነበር ፡ ለምድራዊው ፡ ኑሮ
የሰማዩን ፡ ዓለም ፡ አንዴ ፡ ቢያየው ፡ ኖሮ
ቢበራማ ፡ የተጠራበትን ፡ የክብር ፡ ተስፋ
ቢበራማ ፡ የዘላለም ፡ እርስት ፡ ከቶ ፡ ማይጠፋ
ቢበራማ ፡ ዓይኖቼ ፡ ተከፍቶ ፡ ይህንን ፡ ቢያይ
ቢበራማ ፡ ይናፍቃል ፡ ልቤ ፡ ወደ ፡ ሰማይ
ዓይኖቼን ፡ አብራ ፡ ክፈት ፡ ዓይኔን
እነደ ፡ እኔ ፡ ሳይሆን ፡ እንዳንተ ፡ እንዳይ
ልመናዬ ፡ ይሄ ፡ ነው
አብራው ፡ ዓይኔን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists