Kishore Kumar Hits

Addisalem Assefa - Medane Yigermegnal lyrics

Artist: Addisalem Assefa

album: Sebariw Geta Kefite Wotoal


ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ሲዖል ፡ ሲዘጋ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ሲነጋ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከእስር ፡ ስፈታ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጠላት ፡ ሲመታ (፪x)
ጠላት ፡ ሲመታ (፰x)
ጨለማው ፡ ሲገፈፍ ፡ ብርሃን ፡ ሲበራ (፪x)
አልቆ ፡ ተፈጽሞ ፡ ነገሬ ፡ ሲሰራ (፪x)
በዚያ ፡ የመስቀል ፡ ደም ፡ ሰላም ፡ ሲደረግ (፪x)
እዳዬን ፡ ስከፍለው ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ሲዋጋ (፫x)
ዘንዶ ፡ ተገደለ ፡ ጠላቴ ፡ ተወጋ
ነገር ፡ ተገልብጦ ፡ እኔ ፡ ሰፈር ፡ ነጋ (፪x)
አዝ፦ መዳኔ ፡ ይገርመኛል (፫x)
ታምር ፡ ያሰኘኛል (፪x)
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ሲኦል ፡ ሲዘጋ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ሲነጋ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከእስር ፡ ስፈታ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጠላት ፡ ሲመታ (፪x)
ጠላት ፡ ሲመታ (፰x)
አትሞቺም ፡ ብሎ ፡ ሞቴን ፡ ገደለና (፪x)
በሕይወት ፡ አኖረኝ ፡ ኪዳኑን ፡ አጸና (፪x)
ያ ፡ ባለጋራዬም ፡ ዕቅዱ ፡ ፈረሰ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ በኢየሱስ ፡ ዕንባዬን ፡ አበሰ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ተነሳ (፫x)
መከራዬን ፡ ወስዶ ፡ ሀዘኔን ፡ አስረሳ
መታሰቢያ ፡ አረገ ፡ ሥሙን ፡ እንዳልረሳ (፪x)
አዝ፦ መዳኔ ፡ ይገርመኛል (፫x)
ታምር ፡ ያሰኘኛል (፪x)
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ሲኦል ፡ ሲዘጋ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ሲነጋ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከእስር ፡ ስፈታ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጠላት ፡ ሲመታ (፪x)
ጠላት ፡ ሲመታ (፰x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists