Kishore Kumar Hits

Addisalem Assefa - Endet Eferalehu lyrics

Artist: Addisalem Assefa

album: Sebariw Geta Kefite Wotoal


ተጨንቃ ፡ ለነበረች ፡ ነፍሴ ፡ ጨለማን ፡ አይሆንም ፡ ሲል
አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ሽሮ ፡ መርዶዬን ፡ ሲከለክል
ከፊቴ ፡ ቀድሞ ፡ ሲወጣ ፡ ተራራን ፡ ሲደለድል
ሥራዬን ፡ ሰርቶ ፡ ሲጨርስ ፡ ችግሬን ፡ ሲጠቀልል
መቃብሬን ፡ ሲከፍተው ፡ ታምር ፡ ሲሰራ
ነፍሴን ፡ እጅግ ፡ ሲያስጨንቅ ፡ በእኔ ፡ ሲፈራ
ታምራት ፡ ሲያስለምደኝ ፡ ሲያሳየኝ ፡ ኖሬ
እንዴት ፡ እሸበራለሁ ፡ እፈራለሁ ፡ ዛሬ
አዝ፦ እንዴት ፡ እንዴት ፡ እፈራለሁ (፫x)
ለምን ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ (፫x)
የተሸከመኝ ፡ ትልቅ ፡ አምላክ ፡ ነው (፬x)
ስንቱን ፡ ሸለቆ ፡ ስንቱን ፡ ተራራ
ጥሼ ፡ ሄጃለሁ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ (፪x)
እያሪኮዬ ፡ ቅጥሩ ፡ ሲፈርስ
አይታለች ፡ ነፍሴ ፡ በኢየሱስ (፪x)
ስለዚህ ፡ አልፈራም ፡ ምድር ፡ ብትናወጥ
በዙፋኑ ፡ እያለ ፡ ከቶ ፡ ከቶ ፡ ማይናወጥ (፪x)
በዙፋኑ ፡ እያለ ፡ ከቶ ፡ ከቶ ፡ ማይናወጥ (፪x)
አዝ፦ እንዴት ፡ እንዴት ፡ እፈራለሁ (፫x)
ለምን ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ (፫x)
የተሸከመኝ ፡ ትልቅ ፡ አምላክ ፡ ነው (፬x)
በእሳት ፡ ማሃል ፡ መንገድ ፡ ያለው ፡ ጌታ
መቼ ፡ ትቶኝ ፡ ያውቃል ፡ አንድ ፡ አፍታ
ማዕበልና ፡ ወጀቡን ፡ አራምዶ
ያሻግረኛል ፡ ከባህር ፡ ማዶ
ስለዚህ ፡ አልፈራም ፡ ምድር ፡ ብትናወጥ
በዙፋኑ ፡ እያለ ፡ ከቶ ፡ ከቶ ፡ ማይናወጥ (፪x)
በዙፋኑ ፡ እያለ ፡ ከቶ ፡ ከቶ ፡ የማይናወጥ (፪x)
አዝ፦ እንዴት ፡ እንዴት ፡ እፈራለሁ (፫x)
ለምን ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ (፫x)
የተሸከመኝ ፡ ትልቅ ፡ አምላክ ፡ ነው (፬x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists