Kishore Kumar Hits

Addisalem Assefa - Yetebekut Geta lyrics

Artist: Addisalem Assefa

album: Sebariw Geta Kefite Wotoal


የጠበኩት ፡ ጌታ ፡ ድንገት ፡ ይመጣል (፪x)
አሜን ፡ ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ዉብ ፡ ያደርጋል
የጠበኩት ፡ ጌታ ፡ ድንገት ፡ ይመጣል (፪x)
እሰይ ፡ ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ዉብ ፡ ያደርጋል
ዞር ፡ በል ፡ ጠላቴ ፡ አትነዝንዘኝ ፡ ዞር ፡ በልልኝ
መቼ ፡ ሊረሳኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አባት ፡ የሆነኝ
ስንቱን ፡ አልፌያለሁ ፡ በእርሱ ፡ ብርታት ፡ በጀርባው ፡ አዝሎኝ
አሁንም ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፈጥኖ ፡ ሊረዳኝ
አልተውሽም ፡ ብሎ ፡ ተናግሮኛል
እንደሱ ፡ እውነተኛ ፡ የት ፡ ይገኛል (፪x)
ያስጨበጠንኝ ፡ ቃል ፡ እየዛለሁ
በቃሉ ፡ ይገኛል ፡ አምነዋለሁ
በቃሉ ፡ ይገኛል ፡ አምነዋለሁ (፪x)
ድንገት ፡ ይመጣል ፡ (ድንገት ፡ ይመጣል)
ድንገት ፡ ይመጣል ፡ አሜን
ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ይለውጣል (፫x)
ድንገት ፡ ሲመጣ ፡ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ
እምባን ፡ በማበስ ፡ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ማነው ፡ እንደሱ
ሰብሬ ፡ አልፋለሁ ፡ አሃ ፡ አሃሃ ፡ የነሃሱን ፡ ደጃፍ
መቆም ፡ አልሻም ፡ ከቶ ፡ ጌታ ፡ ስለሚያልፍ
ድንገት ፡ ይመጣል ፡ (ድንገት ፡ ይመጣል)
ድንገት ፡ ይመጣል ፡ አሜን
ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ይለውጣል
ድንገት ፡ ይመጣል ፡ (ድንገት ፡ ይመጣል)
ድንገት ፡ ይመጣል ፡ እሰይ
ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ይለውጣል
እርሱን ፡ ብዬ ፡ የምን ፡ ጭንቀት ፡ እሱን ፡ ብዬ ፡ (እሱን ፡ ብዬ)
ያለስጋት ፡ ልቀመጥ ፡ እንጂ ፡ ተዘልዬ (፪x)
ቢዘገይም ፡ እኮ ፡ በርግጥ ፡ ይመጣል ፡ (ይመጣል)
ሁሉን ፡ ነገሬን ፡ አዲስ ፡ ያደርጋል ፡ (አዲስ ፡ ያደርጋል)
በቀጠረው ፡ ሰዓት ፡ በራሱ ፡ ጊዜ ፡ (በራሱ ፡ ጊዜ)
በእርሱ ፡ ይገሠጻል ፡ ሃዘን ፡ ትካዜ (፪x)
እሱን ፡ ብዬ ፡ የምን ፡ ጭንቀት ፡ እሱን ፡ ብዬ ፡ (እሱን ፡ ብዬ)
ያለስጋት ፡ ልቀመጥ ፡ እንጂ ፡ ተዘልዬ (፪x)
ቢዘገይም ፡ እኮ ፡ በርግጥ ፡ ይመጣል ፡ (ይመጣል)
ሁሉን ፡ ነገሬን ፡ አዲስ ፡ ያደርጋል ፡ (አዲስ ፡ ያደርጋል)
በቀጠረው ፡ ሰዓት ፡ በራሱ ፡ ጊዜ (በራሱ ፡ ጊዜ)
በእርሱ ፡ ይገሠጻል ፡ ሃዘን ፡ ትካዜ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists