Kishore Kumar Hits

Aster Abebe - ይሆንልኛል lyrics

Artist: Aster Abebe

album: ክብር የበቃህ ነህ, Vol. 1


ይሆንልኛል ፡ ይሳካልኛል
ሥጋት ፡ ሰፈሬን ፡ ከራቀ ፡ ሰንበትበት ፡ ብሏል
ይሆንልኛል ፡ ይሳካልኛል
ሥጋት ፡ ሰፈሬን ፡ ከራቀ ፡ ሰንበትበት ፡ ብሏል
ይሆንልኛል ፡ ይሳካልኛል
ሥጋት ፡ ሰፈሬን ፡ ከራቀ ፡ ሰንበትበት ፡ ብሏል
ይሆንልኛል ፡ ይሳካልኛል
ሥጋት ፡ ሰፈሬን ፡ ከራቀ ፡ ሰንበትበት ፡ ብሏል

አልረሳውም ፡ ማንነቴን
በደም ፡ ዋጋ ፡ መገዛቴን
ንጉሥ ፡ ከላይ ፡ ሆኖ ፡ እንዳየኝ
ልጄ ፡ ምርጤ ፡ ርስቴ ፡ እንዳለኝ
አልረሳውም ፡ ማንነቴን
በደም ፡ ዋጋ ፡ መገዛቴን
ንጉሥ ፡ ከላይ ፡ ሆኖ ፡ እንዳየኝ
ልጄ ፡ ምርጤ ፡ ርስቴ ፡ እንዳለኝ
በምሰማው ፡ ሌላ ፡ ውሸት
አልጥለውም ፡ ይህን ፡ ዕውነት
ንጉሥ ፡ ልጁን ፡ የላከልኝ
የተወደድኩ ፡ ምርጥ ፡ ዘር ፡ ነኝ
በምሰማው ፡ ሌላ ፡ ውሸት
አልጥለውም ፡ ይህን ፡ ዕውነት
ንጉሥ ፡ ልጁን ፡ የላከልኝ
የተወደድኩ ፡ ምርጥ ፡ ዘር ፡ ነኝ

አይሆንም ፡ አይሰምርም ፡ ያለው ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ነው?
ሁኔታ ፡ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን ፡ በንጉሥ ፡ ቃል ፡ ሽራለሁ
ተደርጐልኛል ፡ ተሳክቶልኛል ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ
አይሆንም ፡ አይሰምርም ፡ ያለው ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ነው?
ጠላቴ ፡ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን ፡ በንጉሥ ፡ ቃል ፡ ሽራለሁ
ይሆንልኛል ፡ ይሳካልኛል ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ
ቁም ፡ ነገር ፡ አድርጐት ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ
ክብሩን ፡ ሁሉ ፡ ትቶ ፡ ወርዷል ፡ ከላይ
አቅሜን ፡ አውቃለሁ ፡ በእርሱ ፡ ያለኝን
የሆንኩትን ፡ ሆኖ ፡ ያረገኝን
ቁም ፡ ነገር ፡ አድርጐት ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ
ክብሩን ፡ ሁሉ ፡ ትቶ ፡ ወርዷል ፡ ከላይ
አቅሜን ፡ አውቃለሁ ፡ በእርሱ ፡ ያለኝን
የሆንኩትን ፡ ሆኖ ፡ ያረገኝን

ደዌ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ላይሰለጥን፡ እርግማን ፡ በቤቴ ፡ እንዳይገኝ
ዝቅታ ፡ ላይሆንብኝ ፡ በላዬ፡ መሸነፍ ፡ መረታት ፡ ላያገኘኝ
ከፍ ፡ ላለ ፡ ሕይወት ፡ በክርስቶስ ፡ ታጭቻለሁ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ዕጣ ፡ ፈንታዬ
የሆንኩትን ፡ ሁሉ ፡ ሆኖልኛል ፡ በድል ፡ ተፈጽሟል ፡ ጐዳናዬ
ያለቀ ፡ ነው ፡ ያኔ ፡ ድሮ
የእኔ ፡ ጉዳይ ፡ የእኔ ፡ ኑሮ
በቀራኒዮ ፡ ተራራ ፡ ላይ
ተፈጽሟል ፡ ብሎኛል ፡ የእኔ ፡ ጉዳይ

ያለቀ ፡ ነው ፡ ያኔ ፡ ድሮ
የእኔ ፡ ጉዳይ ፡ የእኔ ፡ ኑሮ
በቀራኒዮ ፡ ተራራ ፡ ላይ
ተፈጽሟል ፡ ብሎኛል ፡ የእኔ ፡ ጉዳይ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists