Kishore Kumar Hits

Aster Abebe - እንኻንም አገኘከኝ lyrics

Artist: Aster Abebe

album: ክብር የበቃህ ነህ, Vol. 1


የራቀ ፡ ሰፈሬን ፡ ጠንክሮ ፡ የታጠረ ፡ አጥሬን
ምክንያት ፡ ፈልጎ ፡ ፈጥሮ ፡ የራሱን ፡ ሰበብ
ተቀምጦ ፡ ቆየኝ ፡ ከጉድጓዱ ፡ አጠገብ
የራቀ ፡ ሰፈሬን ፡ ጠንክሮ ፡ የታጠረ ፡ አጥሬን
ምክንያት ፡ ፈልጎ ፡ ፈጥሮ ፡ የራሱን ፡ ሰበብ
ተቀምጦ ፡ ቆየኝ ፡ ከጉድጓዱ ፡ አጠገብ
ሳላውቀው ፡ ማንነቱን ፡ የነፍሴን ፡ መድሃኒት
እንዲህ ፡ እንዲያ ፡ እያልኩኝ ፡ ስደረድር ፡ ምክንያት
ለጥቆ ፡ ገባና ፡ ወደ ፡ ህይወቴ ፡ ባህር
ለራሴው ፡ ነገረኝ ፡ የእራሴን ፡ ሚስጥር
የሚጠጣ ፡ ውሃ ፡ በእኔ ፡ ዘንድ ፡ ፍለጋ
መች ፡ ቆመ ፡ ከደጄ ፡ እራሱን ፡ ሊያረካ
ህይወትን ፡ ሊችረኝ ፡ ከከበቡኝ ፡ ሁሉ
አፋቶ ፡ የእራሱ ፡ አደረገኝ ፡ በፍቅሩ

መስሎኝ ፡ በምድሩ ፡ ሰላምና ፡ እርካታ
ከአንዱ ፡ ተጋብቼ ፡ አንደኛውን ፡ ስፈታ
አይቶ ፡ መባከኔን ፡ በእርግጥ ፡ አዝኖልኛል
በአፉ ፡ ቃል ፡ እፎይታ ፡ ወደ ፡ ቤቴ ፡ ገብቷል
እንኳንም ፡ አገኘኸኝ ፡ አንተ ፡ ወዳጄ
እንኳንም ፡ ቀድመኸኝ ፡ ተገኘህ ፡ ከደጄ
ቢሆንማ ፡ ሌላው
ዛሬን ፡ በአይኔ ፡ ባላየሁ

ቤተ ፡ ዘመድ ፡ ይስማ ፡ ጓደኛ ፡ ጎረቤት
ላፍታም ፡ አልዘገይም ፡ ሳልነግር ፡ ይህን ፡ እውነት
ጉዴን ፡ ለነገረኝ ፡ የኋላ ፡ ታሪኬን
ልቤ ፡ እርሱ ፡ ጋር ፡ ቀርቷል ፡ ወስዶልኝ ፡ ሸክሜን
እንኳንም ፡ አገኘኸኝ ፡ አንተ ፡ ወዳጄ
እንኳንም ፡ ቀድመኸኝ ፡ ተገኘህ ፡ ከደጄ
ቢሆንማ ፡ ሌላው
ዛሬን ፡ በአይኔ ፡ ባላየሁ
ቢሆንማ ፡ ሌላው
ዛሬን ፡ በአይኔ ፡ ባላየሁ
ቢሆንማ ፡ ሌላው
ዛሬን ፡ በአይኔ ፡ ባላየሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists