Kishore Kumar Hits

Aster Abebe - ጌታ ሆይ ተመስገን lyrics

Artist: Aster Abebe

album: ክብር የበቃህ ነህ, Vol. 1

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን
አድናቆት ፡ ያንስሃል ፡ ቢጨመር ፡ ቢጨመር ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን
ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ያንስሃል ፡ ቢጨመር ፡ ቢጨመር ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን

ለመንፈስ ፡ ድኅነቴ ፡ ምስራች ፡ የሰበከ
የልቤን ፡ መሰበር ፡ በቃሉ ፡ እውነት ፡ የጠገነ
ምርኮኛ ፡ የነበርኩትን ፡ ነጻነቴን ፡ ያወጀልኝ
በብዙ ፡ ለቅሶ ፡ ፈንታ ፡ መጽናናትን ፡ የላከልኝ
እጨምራለሁ ፡ ባያክልህ ፡ ባይመጥንም ፡ ጥግህም ፡ ባይደርስም
እጨምራለሁ ፡ ባያክልህ ፡ ባይመጥንም ፡ ጥግህም ፡ ባይደርስም

ለፍቅሬ ፡ መግለጫ ፡ ላድርግ ፡ የቻልኩትን
ጥሜን ፡ ባይቆርጥልኝ ፡ ባያረካም ፡ ውስጤን
ትናንትም ፡ ብያለሁ ፡ ዛሬም ፡ እደግመዋለሁ
መተኪያ ፡ የለህም ፡ እኔ ፡ እወድሃለሁ
ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን
ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን
ሌላ ፡ የለኝም ፡ የሚጨመር ፡ ኢየሱሴ ፡ ተመስገን
ሌላ ፡ የለኝም ፡ የሚጨመር ፡ ኢየሱሴ ፡ ተመስገን

ብዙ ፡ አድርገህልኛል ፡ ከቁጥር ፡ ያለፈ ፡ ከቃላት ፡ ያለፈ ፡ ከንግግር ፡ ያለፈ
ብዙ ፡ አድርገህልኛል ፡ ከቁጥር ፡ ያለፈ ፡ ከቃላት ፡ ያለፈ ፡ ከንግግር ፡ ያለፈ
የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ነህ ፡ የከፍታዬ ፡ ምክንያት ፡ መዳን ፡ የሆንክላት ፡ ላንዷ ፡ ነፍሴ
ወደህ ፡ የተቤዠሃት ፡ ተስፋ ፡ የማደርግህ ፡ ትመጣለህ ፡ ብዬ
የእውነቱን ፡ ልናገር ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ
ኑሮ ፡ መቃብር ፡ ነው ፡ ያላንተ ፡ ኢየሱሴ
የእውነቱን ፡ ልናገር ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ
ኑሮ ፡ አይጥመኝም ፡ ያላንተ ፡ ኢየሱሴ
የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ነህ ፡ የከፍታዬ ፡ ምክንያት ፡ መዳን ፡ የሆንክላት ፡ ላንዷ ፡ ነፍሴ
ወደህ ፡ የተቤዠሃት ፡ ተስፋ ፡ የማደርግህ ፡ ትመጣለህ ፡ ብዬ
የእውነቱን ፡ ልናገር ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ
ኑሮ ፡ አይጥመኝም ፡ ነው ፡ ያላንተ ፡ ኢየሱሴ
የእውነቱን ፡ ልናገር ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ
ኑሮ ፡ አይጥመኝም ፡ ያላንተ ፡ ኢየሱሴ
የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ነህ ፡ የከፍታዬ ፡ ምክንያት ፡ መዳን ፡ የሆንክላት ፡ ላንዷ ፡ ነፍሴ
ወደህ ፡ የተቤዠሃት ፡ ተስፋ ፡ የማደርግህ ፡ ትመጣለህ ፡ ብዬ
የእውነቱን ፡ ልናገር ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ
ኑሮ ፡ መቃብር ፡ ነው ፡ ያላንተ ፡ ኢየሱሴ
የእውነቱን ፡ ልናገር ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ
ኑሮ ፡ አይጥመኝም ፡ ያላንተ ፡ ኢየሱሴ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists