Mahmoud Ahmed - Bemen sebeb letlash lyrics
Artist:
Mahmoud Ahmed
album: Ethiopiques, Vol. 7: Erè mèla mèla 1975-1978
የፍቅር ወጥመድ ነው መላ ሁሉ ገላሽ
ምክንያት አጣሁኝ በምን ሰበብ ልጥላሽ
የፍቅር ወጥመድ ነው መላ ሁሉ ገላሽ
ምክንያት አጣሁኝ በምን ሰበብ ልጥላሽ
♪
በአየንሽ እንዳልጠላሽ ፈራሁኝ ያየኛል
በሚያፈልቀው ጨረር ይመረምረኛል
በጉንጮችሽ ሰበብ ልጠላሽ ፈልጌ
እንጆሪ እንዴት ልጥላ እንደምን አድርጌ
ለማድረግ ፈልጌ ጥርስሽን ምክንያት
ወተት መሰለብኝ ነጣብኝ በማለት
ይህም ሰበብ አይሆንም ልጠላሽ አቃተኝ
ወተት እንዴት ልጥላ ልጅነቴ እምቢ አለኝ
የፍቅር ወጥመድ ነው መላ ሁሉ ገላሽ
ምክንያት አጣሁኝ በምን ሰበብ ልጥላሽ
የፍቅር ወጥመድ ነው መላ ሁሉ ገላሽ
ምክንያት አጣሁኝ በምን ሰበብ ልጥላሽ
♪
ልወድሽ አልወድም ፍቅርሽ አጥፊዬ ነው
በምን ሰበብ ልጥላሽ መጥፎሽ ከምን ላይ ነው
በፀጉርሽ እንዳይሆን ራስሽ ላይ ያለው
ሰው ይስቅብኛል ሀር ተወዳጅ ነው
ልወድሽ አልወድም ፍቅርሽ አጥፊዬ ነው
በምን ሰበብ ልጥላሽ መጥፎሽ ከምን ላይ ነው
በፀጉርሽ እንዳይሆን ራስሽ ላይ ያለው
ሰው ይስቅብኛል ሀር ተወዳጅ ነው
የፍቅር ወጥመድ ነው መላ ሁሉ ገላሽ
ምክንያት አጣሁኝ በምን ሰበብ ልጥላሽ
የፍቅር ወጥመድ ነው መላ ሁሉ ገላሽ
ምክንያት አጣሁኝ በምን ሰበብ ልጥላሽ
ምክንያት አጣሁኝ በምን ሰበብ ልጥላሽ
ምክንያት አጣሁኝ በምን ሰበብ ልጥላሽ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist