Kishore Kumar Hits

Mahmoud Ahmed - Tiz Tiz lyrics

Artist: Mahmoud Ahmed

album: The Best Of... Tizita Vol. 2


ትዝ ትዝ ትዝ እያለኝ
ትዝ ትዝ ትዝ እያለኝ ብዙ ተጨንቄ
ከንቱ ላላገኝሽ አንቺን መናፈቄ
ከንቱ ላላገኝሽ አንቺን መናፈቄ
ህሊናሽ አስቦ
ህሊናሽ አስቦ ልብሽ መቼ ረዳኝ
እኔ ግን ውስጥ ውስጡን መናፈቄ ጎዳኝ
እኔ ግን ውስጥ ውስጡን መናፈቄ ጎዳኝ
መከራን ስችለው ማንም ሰው ሳይረዳኝ
አንቺን መናፈቄ ደህና አድርጎ ጎዳኝ
መከራን ስችለው ማንም ሰው ሳይረዳኝ
አንቺን መናፈቄ ደህና አድርጎ ጎዳኝ
እርሃብ ጥማትም
እርሃብ ጥማትም ምንም አልደፈረኝ
እያንከራተተ እራሴን ያዞረኝ
እያንከራተተ እራሴን ያዞረኝ
ፍችው አልገባኝም
ፍችው አልገባኝም እያልኩኝ ምንድነው
ለካ አንቺን ወድጄ በመናፈቄ ነው
ለካ አንቺን ወድጄ በመናፈቄ ነው
መከራን ስችለው ማንም ሰው ሳይረዳኝ
አንቺን መናፈቄ ደህና አድርጎ ጎዳኝ
መከራን ስችለው ማንም ሰው ሳይረዳኝ
አንቺን መናፈቄ ደህና አድርጎ ጎዳኝ
የፊትሽ ፈገግታ
የፊትሽ ፈገግታ እንደ ጥንቱ መስሎኝ
ስፈልግሽ ብውል ናፍቆት አብሰልስሎኝ
ስፈልግሽ ብውል ናፍቆት አብሰልስሎኝ
ሆኜ ቀረሁ እንጂ
ሆኜ ቀረሁ እንጂ ልቤን አስገማቺ
እንደኔ አፈላላግ መች ተገኘሽ አንቺ
እንደኔ አፈላላግ መች ተገኘሽ አንቺ
መከራን ስችለው ማንም ሰው ሳይረዳኝ
አንቺን መናፈቄ ደህና አድርጎ ጎዳኝ
መከራን ስችለው ማንም ሰው ሳይረዳኝ
አንቺን መናፈቄ ደህና አድርጎ ጎዳኝ
ኧረ በከተማው ጭራሽ በሀገሩ
ከኔና አንቺ በቀር እንማን ነበሩ
ከኔና አንቺ በቀር እንማን ነበሩ
ዛፍ ጥላስር ሆነን ስንመካከር
ከቶ እነማን ሰሙ ስንነጋገር
ከቶ እነማን ሰሙ ስንነጋገር
ጥንት እኔና አንቺ ነን የፍቅር ጀግኖቹ
እነማን ነበሩ ፊት ከዘመኖቹ
ፊት ከዘመኖቹ
ምንስ ግልፅ ቢሆን ግዜና ዘመኑ
ፍቅራችን ተጋልጦ ምነው መመንመኑ
ፍቅራችን ተጋልጦ ምነው መመንመኑ
ኧረ በከተማው ጭራሽ በሀገሩ
ከኔና አንቺ በቀር እንማን ነበሩ
ከኔና አንቺ በቀር እንማን ነበሩ
ዛፍ ጥላስር ሆነን ስንመካከር
ከቶ እነማን ሰሙ ስንነጋገር
ከቶ እነማን ሰሙ ስንነጋገር
ተረስቶሽ እንደሆን ላጫውትሽ ለአንድ ግዜ
እነማን ነበሩ እስኪ በዛን ግዜ እስኪ በዛን ግዜ
እስኪ በዛን ግዜ
አለም ሳይሰለጥን ግዜው ሳይሻሻል
የሰራነው ሁሉ እንዴት ይረሳሻል
የሰራነው ሁሉ እንዴት ይረሳሻል
ኧረ በከተማው ጭራሽ በሀገሩ
ከኔና አንቺ በቀር እንማን ነበሩ
ከኔና አንቺ በቀር እንማን ነበሩ
ዛፍ ጥላስር ሆነን ስንመካከር
ከቶ እነማን ሰሙ ስንነጋገር
ከቶ እነማን ሰሙ ስንነጋገር
ከቶ እነማን ሰሙ ስንነጋገር
ከቶ እነማን ሰሙ ስ ን ነ ጋ ገ ር!!!

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists