Kishore Kumar Hits

Yehunie Belay - Mesganaw Deg New lyrics

Artist: Yehunie Belay

album: Guzara


ይሁኔ በላይ (ምስጋናው ደግ ነው)
ላንቺ ይብላኝ እንጂ ምስጋናውን ላጣሽ
ላንቺ ይብላኝ እንጂ ምስጋናውን ላጣሽ
እኔማ ጠገብኩሽ በህልሜ እየመጣሽ
ምስጋናው ደግ ነው ለእልፍኝ የሚበጅ
ምስጋናው ደግ ነው ለእልፍኝ የሚበጅ
እርጅና በፈረስ ደረሰበት እንጂ
አትዘባበቱ ቀን ጣለው ብላቹህ
ከፊታቹሁ ቆሞ ታገኙታላችሁ
እኔ እየረሳሁት እሱ እያስታወሰኝ
ቸርነቱ እንዲህ ነው እዚህ ያደረሰኝ
ቀብረር
መምህር መቸ ጠፋ ቀሲስና አቡን
እየሳትነው እንጂ ቀን ቆጠራውን
ማን ይጎዳ ብለሽ በኔ ወድቆ መቅረት
የምድርን አይቶ ነው የላይ ቤቱ ምህረት
ያናቀፋኝ ድንጋይ መልሶ ከመታኝ
ሳይጥል አይተወኝም ሱሪ ሳያስፈታኝ
ማን ይጎዳ ብለሽ በኔ ወድቆ መቅረት
የምድርን አይቶ ነው የላይ ቤቱ ምህረት
ልፈወስ ተብሎ ህመም ከተሻረ
ይጠጣ የለም ወይ ኮሶ እየመረረ
አንዳንድ ቀን ዘራፍ ልበል እንጂ እንደ ወንድ
ወተት ብቻ እኮነው መገፋት የሚወድ
ከልክለሺኝ እንጂ ሰርቼ እንዳልበላ
መች ይጠፋኝ ነበር የግብርናው መላ
ወይ አትሰበስቢኝ ወይ ትተሽ አተይኝ
እንደ መና ጥጃ ዛሬም አስከትይኝ
አዙሪት ነው መሰል እግሪን የያዘው
ዞሪ ዞሪ ደጅሽ ተመልሼ እዛው
እስቲ ፈልጉልኝ የማምሳይ ወተት
ከሷ ጋር ስብሃት የምደግምበት
ይሄን ጥሩ ሙያ ከቶ የት ተማርሺው
ስንቱን ጎበዝ ጀግና ወዶ ገብ አረግሺው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists