Kishore Kumar Hits

Temesgen Gebregziabher - Kebad lyrics

Artist: Temesgen Gebregziabher

album: Kebad


ከባድ ነው መኖር ያላንቺ
ከባድ ነው መኖር ካንቺ ጋር
የረዘመ ሌት ሲሉ አይነጋም
ደግም ያጠረ ቀን አንሶ አይበቃም
ፍቅርሽ በመናው ልቤ ገብቶ
መስኮት ይከፍታል በሩን ዘግቶ
ለመሄደሰ ማሰብ አንቺን ጥሎ
ከባድ ሆነብኝ ቀላል መስሎ
ሳዝን ለልቧ ለወደደኝ
መሣቅ አይድል ወይ የከበደኝ
ባንድ የኖሩለት ዉሀና እሳት
ከባድ አይድል ወይ ቀላል ማሣት
ብቻዬን ልኑር ብል ያላንቺ
ኦና ነው ቤቴም አይመቺ
ከባድ ነው መኖር ያላንቺ
ልቤን አልኩና በሷው እርጋ
ብታገስ ሌቱም እሥኪነጋ
ከባድ ነው መኖር ካንቺ ጋ
ከባድ
ከባድ ነው መኖር ያላንቺ
ከባድ ነው መኖር ካንቺ ጋር
ነው እንዴ ያለሤት እራሱ ሲያጥር
አምስት የሌለው ሀምሣ ቁጥር
ነጭ ያለ ጥቁር መች ይፈካል
ሣይኖር ጨለማ እንዴት ይነጋል
ድሥት ያለ ክዳን ላይሆን እቃ
ምንም አይቀናኝ ተውኩሽ በቃ
አስራኝ ከቅርቧ ግራና ቀኝ
መራቅ አይደል ወይ የከበደኝ
ወተት ቢታገስ መቻል አውቆ
ይሆናል ቅቤ ተነቅንቆ
ብቻዬን ልኑር ብል ያላንቺ
ኦና ነው ቤቴም አይመቺ
ከባድ ነው መኖር ያላንቺ
ልቤን አልኩና በሷው እርጋ
ብታገስ ሌቱም እሥኪነጋ
ከባድ ነው መኖር ካንቺ ጋ
ከባድ
The end

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists