የኔማ ልጅ ሚካኤል
ልጅ ሚካኤል ብላለች እናቱ ስም አዉቃ
የረከሰ አይነካም እንደ ታቦት እቃ
የኔማ ልጅ ሚካኤል አንተን የወለደች ባየዋት እናትህን
የተሞላ ቢራ አስመስላ አንገትክን
የእንግሊዝ ብረጭቆ አስመስላ አንገትክን
የኔማ ልጅ ሚካኤል
እኔስ ለገንዘብህ ስም አታረግብኝ
በሄድክበት ቦታ ደና ሁንልኝ
የኔ አድለ መልካም የኔ ስመ መልካም
በእግሩ ፍሬን እንጂ በአፉ ሰዉ አይነካም
የኔማ ልጅ ሚካኤል
ሰማይ ልኩ ኮከብ ሰማይ ልኩ ኮከብ አጥማቂዉ ጨረቃ
ቅዱስ ሚካኤል ነዉ ያንተ ዋስ ጠበቃ
መላዕኩ ገብርኤል ነዉ ያንተ ዋስ ጠበቃ
እስከመጣሁባት ምድር
ሰዉን ከማስደሰት በቀር
አይወጣኝም ክፉ ነገር
የጥሩ ሰዉ ዜማ ከላይ ተሰቀለ
መኖር ነበረባት ብዙነሽ በቀለ
የኩባያ ወተት የለዉም አረፋ
በሽታዬን የሚያቅ አስታማሚ ጠፋ
ጥሩ ሰዉ ከለየ በዳሰሳ መልኩ
ተሾመ አሰግድ የጥበብ ሰዉ ልኩ
ከዚ በላይ ጥበብ ከየት ይመጣል ልኩ
ልበ ብርሃን ሲባል ትርጉሙ ካልገባሽ
ዉረጅ ተመለሺ ቢሉሽም የት ነበርሽ
የት ነበርሽ
ቢሳካ መንገዴ ዳር እና መሀሉ
ሲገምቱኝ ዉለዉ በስም እየማሉ
ሚስጥረኛ መፅሀፍ አንብቦ ነዉ አሉ
ገረመኝ ስሰማ መወራረዳቸዉ
ሚተካዉ አይጠፋም እሱን ማለታቸዉ አዬ
ተወራረድ ተብሎ ቢሰጠኝ እድል
ባለኝም በሌለኝ ብያዝም ወገቤ
እወራረዳለዉ ደግሜ ደግሜ
ባህሩ ቃኜንስ አይተኩትም ብዬ
አባ ወዴ ሰማው ቆመዋል ወይ ከበሬ
ሊሞገስ ነዉ መሰል ዉሎና አዳሬ
እሽት እሽት አርገዉ ጤናዳም በሻይ
ጨብጠዉ ሚሄደዉ በረካ ነዉ ወይ
ገበታ በመሶብ ሳይዘጋ በር
ልማድሽ ነበረ ከጎረቤት ጋር
ከራስሽ የዉጣ ስምሽን የማይጠራ
ከገበታዉ ዘሩን ጀመረ ቆጠራ
እኔ አላዉቅልሽም አልልም እርግማን
ብቻ አደራሽን ደግመሽ እንዳትወልጅው
ከዘርም ዘር አለ የሚበላ እንደገብስ
ሰዉ እንዴት በዘሩ ይበላል የሰዉ ነፍስ
ይታረሳል መሬት ኧረ በላይ በላይ
ከዛ እስከዚ ድረስ መጣዉ በሬሳ ላይ
ወዴት ሄደ በሬዉ የቦታዉ አለቃ
አጋቹስ ምን ሆነ ተኝቶ ማይነቃ
ጠጥቶ ነዉ አሉኝ ያንን ካቲካላ
እኛ አናቅም አሉ ዳሂራ እንደጠጣ
ሰዉ ሀገር ወዳድ አይደል ልበ ገራገሩ
ያልበጁለት ሴራ ከበር እስከ በሩ
ለዉሰዉ ቢሰጡት ክፋትን በማሩ
ከክፋቱ በላይ አረ ጎላ ማሩ
እስከመጣሁባት ምድር
ሰዉን ከማስደሰት በቀር
አይወጣኝም ክፉ ነገር
የጥሩ ሰዉ ዜማ ከላይ ተሰቀለ
ብትኖር ጥሩ ነበር ብዙዬ በቀለ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist