Kishore Kumar Hits

Lij Michael - Zemenay Mariye lyrics

Artist: Lij Michael

album: Zaray Yehun Nege


ሃሃሃ fellas
ሃሃ rockin' out to late
ማናት እሷ ፣ እቺ?
እህ ዘመናይ ማርዬ
እህ እህ yeah
የጨዋ ልጅ ሽቅርቅር
አንቺ ቆንጆ የኔ ማር
ንጉስ ቆመ ከወንበሩ
መጣሽ ተብሎ ቢናገሩ
እናት ሲሉሽ ልጅ እግር
አባት ሲሉሽ ውክብክቤ
እኔም አልኩሽ በተራዬ
ሽቅርቅሯ አ
ዘመናይ ማርዬ
እሷ ዘመናይ ፣ እሷ ማርዬ
ልቤ ሳሳላት ፣ ልጥራት ማን ብዬ?
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ድግስ ተደገሰ ፣ ግብር ተጣለልሽ
ካባ ላይ ቁጭ ብለው ፣ እናትና አባትሽ
እልፍኙም ተሞላ ፣ አንቺም ደስ ይበልሽ
ሎሌ ለባላባት ፣ ሁሉም ተጠራልሽ
ጉርሻና ምርቃት ፣ ቢወርድም በላይሽ
ቢያንስ ነው እንጅ ፣ መቼም አይበዛብሽ
ቢረጥብ ብደላው ፣ ድርቅ ያለ መሬት
ሽር በይ በሞቴ ፣ ተመላለሺበት
እንደ ልእልቲቷ ፣ እንደ ዘውዲቱ ቤት
ባለሟሉ ብዙ ፣ ሚነጠፈው መሬት
እንደ ማሩ ሰፈፍ ፣ እንደ ወርቁ ዱካ
ሀገሬው በሙሉ ፣ ይወድሻል ለካ (ሃሃሃ yeah)
የጨዋ ልጅ ሽቅርቅር
አንቺ ቆንጆ የኔ ማር
ንጉስ ቆመ ከወንበሩ
መጣሽ ተብሎ ቢናገሩ
እናት ሲሉሽ ልጅ እግር
አባት ሲሉሽ ውክብክቤ
እኔም አልኩሽ በተራዬ
ሽቅርቅሯ አ
ዘመናይ ማርዬ
እሷ ዘመናይ ፣ እሷ ማርዬ
ልቤ ሳሳላት ፣ ልጥራት ማን ብዬ?
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
እግዜር በአምሳሉ እንደዚ የሰራሽ
የኔን ብቸኝነት ይርሳ ብሎ የላከሽ
የሳቄ መክፈቻ አይኔን እማይብሽ
ካፈሩ ከሸክላው ከውሃው የሰራሽ
ለኔም ሽልማቴ ለሱም ትዛዙ ነሽ
እኔ አንቺን ባላገኝ ምሽቱ ተከፋ
ጨረቃ አኮረፈች ኮከብ ሁሉ ጠፋ
መሬቱም ደረቀ ሰማዩም ተቆጣ
እንግዲህ ይሄ ነው አንቺን ወዶ ላጣ
አንቺ ነይ ዘመናይ የቤቱ ዘናሚት
ለደከመው ጉልበት ለመመው መዳኒት
ግቢና ከፊቴ ይብዛም በረከቴ
አንድም ለስጋ ነው አንድም ለሂወቴ
እኔ እወድሻለው ውደጅኝ በሞቴ (ሃሃሃ yeah)
የጨዋ ልጅ ሽቅርቅር
አንቺ ቆንጆ የኔ ማር
ንጉስ ቆመ ከወንበሩ
መጣሽ ተብሎ ቢናገሩ
እናት ሲሉሽ ልጅ እግር
አባት ሲሉሽ ውክብክቤ
እኔም አልኩሽ በተራዬ
ሽቅርቅሯ አ
ዘመናይ ማርዬ
እሷ ዘመናይ ፣ እሷ ማርዬ
ልቤ ሳሳላት ፣ ልጥራት ማን ብዬ?
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ዘመናይ ማርዬ ፣ እህ
ሃሃ yeah
ዘመናይ ማርዬ
ሃሃሃ ፣ ላክነው
አህ (ኤይ ኤይ ኤይ)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists