Kishore Kumar Hits

Lij Michael - Agerem Endi lyrics

Artist: Lij Michael

album: Zaray Yehun Nege


ኣኸኸኸ ፋፍ!
Yeah
ብላክ ኖት!
ሁኔ!
Yeah!
ሀገርም እንዲህ ሰውም እንደኛ
አለማ ካሉ እስቲ ይምጡ ወደኛ
በል እርገጥ እርገጥ ጎበዝ እርገጠው
የሀገሬ መሬት እሾህም የለው
በል ቀና ቀና ቀና ከአንገትህ
ማንን ልትፈራ ደግሞ በእናትህ ቤት
ሀገርም እንዲህ ሰውም እንደኛ
አለማ ካሉ እስቲ ይምጡ ወደኛ
ሰላም ሰላም እንደምንድናችሁ
ፍቅር እና ጤና ይግባ ከቤታችሁ
ደህና ደህና
ቤተሰብ ዘመዱስ ሁሉም አሸወይና
እሸት እሸት
ከጥግ እስከ ጥግ ሁሉም ይመርበት
ግባ ጨፍር ተጫወት እንደኛ
ምን ትተክዛለህ ሀገሩ እንደውን የኛ
ዋልም እደር ምንም ሳትከፋ
ዛሬን አጣሁ ብለህ አይዞህ አንገትህን አትድፋ
ቢሰማ ቢነገርም አያልቅበት
ሀገርማ እዚህ ነው እኛ ያለንበት
በሀዘንም በደስታ ሰው ማናጣበት
ቤትስ ኢትዮጵያ ናት የምርም እናት

እኅቴ ምንድነው ግቢና ጨፍሪ
በዚህ በደስታ ቀን ደስ ይበልሽ ኩሪ
እኔም የሀገርሽ ልጅ የራፑ አዝማሪ
ክልሉ የኛው ነው ማንንም አትፍሪ
ሃ! Yeah!
ሀገርም እንዲህ ሰውም እንደኛ
አለማ ካሉ እስቲ ይምጡ ወደኛ
በል እርገጥ እርገጥ ጎበዝ እርገጠው
የሀገሬ መሬት እሾህም የለው
በል ቀና ቀና ቀና ከአንገትህ
ማንን ልትፈራ ደግሞ በእናትህ ቤት
ሀገርም እንዲህ ሰውም እንደኛ
አለማ ካሉ እስቲ ይምጡ ወደኛ
ሰሜን ደቡብ ምዕራብና ምሥራቅ
ሰላም ፍቅር ሁሌም ከኛ አይራቅ
አማን አማን
ቸር ብላችሁ ሸኙን ያገር ሹማምንታን
ሃ!
እዚም እዛም የትም
ጎረቤት ሀገሩም ይሁን ደጀሰላም
ፍቅር መውደድ መቻል እና ትዕግስት
ሀገር ወገን ባንዲራና እምነት
ድሮም ከጥንት ነው የኛማ አንድነት
ሃ!
እስኪ እንጨዋወት ምን አለ ልባችሁ
ዘመድ ጓደኞቼ ከሀገር የወጣችሁ
ሃሳቡም እቅዱም ተሳክቶ ህልማችሁ
እስክትመለሱ ሆድ እንዳይብሳችሁ
ቅርብ ነው አይርቅም መንገዱ ሁሉ ቀና
ሁሉም ተሰባስቦ ሀገሩ ይገባና
ከፅዋው ከጻዲቅ እንቀማምስና
በእሪኩም ዘመዳ በአንቺሆዬ ናና
ኧረ እኔ ነኝ ባሉም ይሸከሸክና
ምን አለኝ ሀገሬ ይዘፈናል ገና
ሃ! Yeah!
ገና ለገና ምታ መሰንቆ
እንዴት ይቻለው ሆዴ ካንቺማ ርቆ
ገና ለገና ምታ መሰንቆ
እንዴት ይቻለው ሆዴ ካንቺማ ርቆ
ገና ለገና ምታ መሰንቆ
እንዴት ይቻለው ልቤ ካንቺማ ርቆ
ገና ለገና ምታ መሰንቆ
እንዴት ይቻለው ልቤ ካንቺማ ርቆ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists