Kishore Kumar Hits

Yohana - Ha lyrics

Artist: Yohana

album: Ereft


You ready
Yah me ready
Gimmie da riddim
And let's play some real reagge music

ቃል ትልቅ ነው ያለማል ያጠፋል አምናለው
ሁን ተማሪ ከቶ አትበል ደርሼ አውቃለው
ላይሮር ፍፁም ላይኖር ሙሉ ላይኖር ኦና
እይ ስተትክን ልብ ብለህ ከሚያቀና
ካንተ በላይ የለም ሲሉኝ መች አምናለው
ቢሉ አታውቅም አይረብሸኝ ውስጤን አውቃለው
ማለት እህ የለው ክፋት ሁሉን ሰማለው
ግን ተስማምቶኝ የዋጥኩትን እኔ አውቃለው
አይረፍድም ሲሆን ሊያውቁ መጠየቅ አይገድም
ያያል እውነቱን ሰው ሊሊህ ባይወድም
አላውቅም ባለጠያቂም አይፈርድም
ግን እምቢ ይልና አለማወቅ በድርቀት ላይቀና
ምገነባውም ላይቆም ላይፀና
ጆሮ ይነሳል ያልታረመ ያልሰማ
ብልህ ሀ ሞኙ ዋ ብሎ በግዜ ይማራል
አዝናለው ሙሉ ነኝ ላለ በምን ይድናል
ብልህ ሀ ሞኙ ዋ ብሎ በግዜ ይማራል
አዝናለው ሙሉ ነኝ ላለ በምን ይድናል

ግዴታ አይደል ማወቅ ሁሉን ስጠይቅም በል ቀና
ለማስተማር መማር ከልብ ለመቆምም ዳዴ አለና
ግዴታ አይደል ማወቅ ሁሉን ስጠይቅም በል ቀና
ሳትገደድ በመዘዝከው በአፍህ ሳይመጣ ፈተና
አይረፍድም ሲሆን ሊያውቁ መጠየቅ አይገድም
ያያል እውነቱን ሰው ሊሊህ ባይወድም
አላውቅም ባለጠያቂም አይፈርድም
ግን እምቢ ይልና አለማወቅ በድርቀት ላይቀና
ምገነባውም ላይቆም ላይፀና
ጆሮ ይነሳል ያልታረመ ያልሰማ
ብልህ ሀ ሞኙ ዋ ብሎ በግዜ ይማራል
አዝናለው ሙሉ ነኝ ላለ በምን ይድናል
ብልህ ሀ ሞኙ ዋ ብሎ በግዜ ይማራል
አዝናለው ሙሉ ነኝ ላለ በምን ይድናል

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists