Kishore Kumar Hits

Yohana - Endelbua lyrics

Artist: Yohana

album: Endelbua


አይገደን የመጠን ስፋት ጥበቷ (ጥበቷ)
ጎጇችን ግልፅነት ጌጧ ውበቷ
ላይጠቁም ያንተ ባይ የሷም ሰው ላይገባ
ሳላይ ፍፁም ሌላ ሳይርቅ ከኔ ቀልቧ
ግማሽ በሀሳቧ ሄጄ ለኔም ግማሽ ቀርባ
የኛ ቤት የኛ ነው ነው እንደልቤ እንደልቧ
ላይጠቁም ያንተ ባይ የሷም ሰው ላይገባ
ሳላይ ፍፁም ሌላ ሳይርቅ ከኔ ቀልቧ
ግማሽ በሀሳቧ ሄጄ ለኔም ግማሽ ቀርባ
የኛ ቤት የኛ ነው ነው እንደልቤ እንደልቧ
በግፊት ያልመጣ ፍቅራችን በምልጃ
ሆኖ በኔ በሷ ፍፁም ይሁን ፍርጃ
ከእኔ ከእሷ ውጪ ሳታደርስ ደጇ
ጣልቃም ገቢ ሳይኖር ብለን እንጃ እንጃ
ትቶ ጎረቤቱን ሰው ሊኖር እንደቤቱ
ያስገድደዋል አለም ያስገድዳል እውነቱ
ሁሉም እንደዕውቀቱ ሲሆን ማገር ለቤቱ
ያወጣል ከመንቀዥቀዥ ያዋጣዋልም ቤቱ
ወላጅነት መልካም ጓዳ አልፎ ካልነካን
ወዳጅነት ጥሩ ቤት ካላለካካን
አይቅርብን ያረጉት ቅብጠት ያልነካካን
ላይሰፋን ላይጠበን ነን በልክ የለካን
አይገደን የመጠን ስፋት ጥበቷ (ጥበቷ)
ጎጇችን ግልፅነት ጌጧ ውበቷ
ላይጠቁም ያንተ ባይ የሷም ሰው ላይገባ
ሳላይ ፍፁም ሌላ ሳይርቅ ከኔ ቀልቧ
ግማሽ በሀሳቧ ሄጄ ለኔም ግማሽ ቀርባ
የኛ ቤት የኛ ነው ነው እንደልቤ እንደልቧ
ላይጠቁም ያንተ ባይ የሷም ሰው ላይገባ
ሳላይ ፍፁም ሌላ ሳይርቅ ከኔ ቀልቧ
ግማሽ በሀሳቧ ሄጄ ለኔም ግማሽ ቀርባ
የኛ ቤት የኛ ነው ነው እንደልቤ እንደልቧ
የራስ መንገድ አይቶ ጎጆ መስራት እንጂ
አብሮ ከማይኖር ሰው ደግሞ ምን ሊረባ ቅጂ
ጀርባስ ለምን ይሰጥ ልሁን ላለ ነጂ
ያበዛ አይን ኑሮ ውሎ አድሮ ከርሞ ሊል እጅ እጅ
ትቶ ጎረቤቱን ሰው ሊኖር እንደቤቱ
ያስገድደዋል አለም ያስገድዳል እውነቱ
ሁሉም እንደዕውቀቱ ሲሆን ማገር ለቤቱ
ያዋጣል ከመንቀዥቀዥ ያዋጣዋልም ቤቱ
ወላጅነት መልካም ጓዳ አልፎ ካልነካን
ወዳጅነት ጥሩ ቤት ካላለካካን
አይቅርብን ያረጉት ቅብጠት ያልነካካን
ላይሰፋን ላይጠበን ነን በልክ የለካን
አይገደን የመጠን ስፋት ጥበቷ (ጥበቷ)
ጎጇችን ግልፅነት ጌጧ ውበቷ
አይገደን የመጠን ስፋት ጥበቷ (ጥበቷ)
ጎጇችን ግልፅነት ጌጧ ውበቷ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists