Kishore Kumar Hits

Yohana - Addis lyrics

Artist: Yohana

album: Addis


አውቀህ በድፍረት
ሳታውቅ በስህተት
ያጠፋኸውን ባንተ መንገድ
ደግሞ እንዳይመጣ
በል በደንብ ጥረግ
የአዲሱን ትውልድ መንገድ
አውቀህ በድፍረት
ሳታውቅ በስህተት
ያጠፋኸውን ባንተ መንገድ
ደግሞ እንዳይመጣ
በል በደንብ ጥረግ
የአዲሱን ትውልድ መንገድ
የአዲስ ትውልዱም ሚና
አልገባኝም እኔ ገና
አዲስ ትውልድ ነኝ ባዩም
አስረዳኝ ለኔ በናትህ
LoganS ቢቀየር ዛሬም
አለባበስ ወይ ተግባርም
የዛሬንም ትርምስ
አይቸው ነበር ትላንት
ያለፈን ምታገኘው
በልጅህ አዲስ ህይወት ነው
የተሻለች አለም ብትሻ
ፊቱን ማሳየት ለርሱ ነው
ፍቅርን ክብርን እውነትን
ማስተዋልን እውቀትን
እንዲኖር ከልቡ አስቦ
አፍርሶ የራስ ስህተትን
መገንባት ነው ውብ ቤትን
ንፁህ አብኩቶ ካብ ክቦ
አዲስ አዲስ ነው
የአዲስ ትውልድ ኑሮ
አዲስ አዲስ ነው
የአዲስ ትውልድ ኑሮ
አዲስ አዲስ ነው
የአዲስ ትውልድ ኑሮ
አዲስ አዲስ ነው
የአዲስ ትውልድ ኑሮ
አውቀህ በድፍረት
ሳታውቅ በስህተት
ያጠፋኸውን ባንተ መንገድ
ደግሞ እንዳይመጣ
በል በደንብ ጥረግ
የአዲሱን ትውልድ መንገድ
አውቀህ በድፍረት
ሳታውቅ በስህተት
ያጠፋኸውን ባንተ መንገድ
ደግሞ እንዳይመጣ
በል በደንብ ጥረግ
የአዲሱን ትውልድ መንገድ
በጎ አስተሳሰብ እንጂ
ጫጩትነት አይደለም
ከአልጨበጥ ባይ ጮሌነት
የሚያፋታንስ ከልብም
የትላንቱ ሰው በራሱ ቤት አዲስ ሰው ነበረ
አለፈበት እንጂ እሱም እኮ
አምፆም ነበረ
በየዘመኑ አዲስ ትውልድ
አዲስ መንፈስ ቢፈጠር
እውነት ምንግዜም ያው ነች
አካባቢም ቢቀየር
በየዘመኑ አዲስ ትውልድ
አዲስ መንፈስ ቢፈጠር
እውነት ምንግዜም ያው ነች
አካባቢም ቢቀየር
ስህተትህ ይስጠው ብልሀቱን (ያዲስ ትውልድ ሚና)
እውቀትህ ይሁን ብርታቱ (አልገባኝም እኔ ገና)
መፍትሄህ ይሁን እውነቱ(አዲስ ትውልድ ነኝ ባዩም)
ህይወትህ ይሁን መብራቱ(አስረዳኝ ለኔ በናትህ)
አዲስ አዲስ ነው
የአዲስ ትውልድ ኑሮ
አዲስ አዲስ ነው
የአዲስ ትውልድ ኑሮ
አዲስ አዲስ ነው
የአዲስ ትውልድ ኑሮ
አዲስ አዲስ ነው
የአዲስ ትውልድ ኑሮ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists