Kishore Kumar Hits

Yohana - Weshetwan New lyrics

Artist: Yohana

album: Yohana


ኦ ውሸቷን ነው
የደላት መስላለች
ኦ እንዳይከፋኝ ነው አውቃለው
ጉዳቷን ውጣለች
ኦ ውሸቷን ነው
የደላት መስላለች
ኦ እንዳይከፋኝ ነው አውቃለው
የኛ ትንሽ ሕመም ካንጀትሽ ይውላል
ምን ቢያንስ ምን ቢቀል
ተኝተን ማታምኚን
የፀሎትሽ ማገር ሁልጊዜ ሌተቀን
ቢያልፍ እጅሽ በሰንበት ጾመኛ ሆነሽ
ጠግበን ዋልን ልጆችሽ (ኦአ)
ልብ አጥተን ጎርምሰን ብንፈጅሽ
አለሽ ልጆቼ ትያለሽ (ኡኡ)
ኦ ውሸቷን ነው
የደላት መስላለች
ኦ እንዳይከፋኝ ነው አውቃለው
ጉዳቷን ውጣለች
ኦ ውሸቷን ነው
የደላት መስላለች
ኦ እንዳይከፋኝ ነው አውቃለው
እማማ
አይ መውለድ ብቻ አይደለም የእናትነት ምስጢሩ
እማማ
ማሳደግ ነው አቅፎ ሳያየው ያን ችግሩን
እማማ
ማማጥ መውለድ ብቻ እናት ሚያስብል አይደለም
እማማ
ያሳደገም አቅፎ ስሙ የሚበዛ አልሆነም
እማማ
መኖርን ብመርጥ ለጥበብ ፈቀቅ ብዬ ከመንገድሽ
እማማ
ሳላውቀው ነው ውስጤ ገብቶ ጥንካሬሽ ያ ድፍረትሽ
እማማ
የልብሽ ደረሰ ዳዴውን ትቶ ቆመልሽ
እማማ
ምን ልታዘዝ ምን ልታዘዝ ደረስኩልሽ
ደርሻለው (ሄይ)
ደርሻለው (ሄይ)
ምን ልታዘዝ እልሻለው (ሄይ)
እማ ደርሻለው ደርሻለው (ሄይ)
ምን ልታዘዝ እልሻለው (ሄይ)
ኦ ውሸቷን ነው
ኦ እንዳይከፋኝ ነው
አውቃለው (ኦኡኦኦ)
አውቃለው (ኡኡኦኡኡ)
እማማ (ኡኡኦኡኡ)
እማማ (ኡኡኦኡኡ)
እማማ (ኡኡኦኡኡ)
እማማ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists